إعدادات العرض
አላህ ሆይ! እኔ ከቀብር ቅጣት፣ ከእሳት ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተና እና ከመሲሕ ደጃል ፈተና ባንተው እጠበቃለሁ።'
አላህ ሆይ! እኔ ከቀብር ቅጣት፣ ከእሳት ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተና እና ከመሲሕ ደጃል ፈተና ባንተው እጠበቃለሁ።'
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና): 'አሏሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዓዛቢል ቀብሪ ወሚን ዓዛቢ‐ን‐ናር ወሚን ፊትነቲል መሕያ ወል መማት ወሚን ፊትነቲል መሲሒ‐ድ‐ደጃል' እያሉ ዱዓእ ያደርጉ ነበር።" 'ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከቀብር ቅጣት፣ ከእሳት ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተና እና ከመሲሕ ደጃል ፈተና ባንተው እጠበቃለሁ።' ማለት ነው። በሙስሊም ዘገባ ደግሞ 'አንዳችሁ ከመጨረሻው ተሸሁድ ያጠናቀቀ ጊዜ ከአራት ነገሮች በአላህ ይጠበቅ: ከጀሀነም ቅጣት፣ ከቀብር ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተናና ከመሲሕ ደጃል ክፋት።'ብለዋል።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî Kiswahili සිංහල Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Tiếng Việt پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or नेपाली Kinyarwanda Română తెలుగు Lietuvių Oromoo മലയാളം Nederlands Soomaali Српски Українська Deutsch ಕನ್ನಡ Wolof Moore Shqip ქართული Azərbaycan Magyar தமிழ் Македонски မြန်မာ Malagasyالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመጨረሻው ተሸሁድ በኋላ ከሶላት ከማሰላመታቸው በፊት ከአራት ነገሮች በአላህ ይጠበቁ ነበር። እኛንም በአላህ ከነርሱ እንድንጠበቅ አዘዙን። የመጀመሪያው: ከቀብር ቅጣት ነው። ሁለተኛው: የትንሳኤ ቀን ከእሳት ቅጣት ነው። ሶስተኛው: ከህይወት ፈተናዎች ሲባል ክልክል ከሆኑ ዓለማዊ ዝንባሌዎችና አጥማሚ ማደናገሪያዎች፤ እንዲሁም በሞት ሰአት ከሚያጋጥሙ ፈተናዎች ሲባል ደግሞ በጣእረ ሞት ሰአት ከኢስላም ወይም ሱና መጥመምን የመሰሉ ወይም በሁለቱ መላእክት መጠየቅን ከመሰለ የቀብር ፈተና ማለት ነው። አራተኛ: በመጨረሻ ዘመን የሚወጣ ከሆነው ከመሲሕ ደጃል ፈተና ነው። አላህ በርሱ አማካኝነት ባሮቹን ይፈትናል። ዱዓው ላይ እርሱ ተለይቶ የተጠቀሰው የርሱ ፈተናና ማጥመሙ ከባድ ስለሆነ ነው።فوائد الحديث
ይህ መጠበቂያ ዱዓ ከዱንያና ከመጨረሻው ዓለም ክፋቶች መጠበቅን ከሰበሰበ አንገብጋቢና ጠቅላይ ከሆነ ዱዓዎች መካከል አንዱ ነው።
የቀብር ቅጣት የተረጋገጠና እውነት መሆኑን እንረዳለን።
የፈተናን አደገኝነት እና ከፈተና ለመዳን በአላህ መታገዝና ዱዓ ማድረግ እንደሚገባ እንረዳለን።
የደጃል መውጣት የተረጋገጠ መሆኑንና ፈተናው ከባድ መሆኑን እንረዳለን።
ከመጨረሻው ተሸሁድ በኋላ ይህን ዱዓ ማለት እንደሚወደድ እንረዳለን።
ከመልካም ስራ በኋላ ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
التصنيفات
የሶላት አዝካሮች