إعدادات العرض
የጁሙዐ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ሳለ ለባልደረባህ 'ዝም በል!' ካልከው በርግጥም ውድቅ ንግግርን ተናግረሀል።
የጁሙዐ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ሳለ ለባልደረባህ 'ዝም በል!' ካልከው በርግጥም ውድቅ ንግግርን ተናግረሀል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "የጁሙዐ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ሳለ ለባልደረባህ 'ዝም በል!' ካልከው በርግጥም ውድቅ ንግግርን ተናግረሀል።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands සිංහල தமிழ் ไทย دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली Malagasy Italiano or ಕನ್ನಡ Oromoo Română Soomaali Српски Wolof Українська Moore Azərbaycan ქართული Magyarالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የጁሙዓ ኹጥባ ላይ የተሳተፈ ሰው ሊያሟላቸው ከሚገባ ግዴታ ስርዐቶች መካከል ተግሳፁን ሊያስተነትን ዘንድ ኹጥባ አድራጊውን በጥሞና ማዳመጥ እንደሚገባ ግልፅ አደረጉ። ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ለሌላ ሰው "ዝም በል!" "አዳምጥ!" እንደማለት ትንሽ ነገር እንኳ ያወራ ሰውም ቢሆን የጁመዐ ሶላት ትሩፋት አምልጦታል።فوائد الحديث
ኹጥባ በሚደመጥበት ወቅት መጥፎን ማውገዝ ወይም ሰላምታን መመለስና ያስነጠሰን "የርሐሙከላህ" ማለትን እንኳ ቢሆን ማንኛውም ንግግር መናገር ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
ኢማሙን የሚያወራ ወይም ኢማሙ የሚያወራው ሰው እዚህ ክልከላ ውስጥ አይካተትም።
አስፈላጊ ከሆነ በሁለቱ ኹጥባዎች መካከል ማውራት ይፈቀዳል።
ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከተወሱ ድምፅህን ቀንሰህ በሳቸው ላይ ሶላትና ሰላም ታወርዳለህ። ልክ እንደዚሁ ዱዓ ሲደረግም በዝግታ (ድምፅህን ቀንሰህ) አሚን ትላለህ።
التصنيفات
የጁሙዓ ሶላት