إعدادات العرض
አምስቱ ከተፈጥሯዊ (ኢስላማዊ ሱናዎች) ናቸው፦ መገረዝ፣ የብልትን ፀጉር መላጨት፣ ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለን ፂም) ማሳጠር፣ ጥፍሮችን መቁረጥና የብብትን ፀጉር መንጨት ።
አምስቱ ከተፈጥሯዊ (ኢስላማዊ ሱናዎች) ናቸው፦ መገረዝ፣ የብልትን ፀጉር መላጨት፣ ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለን ፂም) ማሳጠር፣ ጥፍሮችን መቁረጥና የብብትን ፀጉር መንጨት ።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "አምስቱ ከተፈጥሯዊ (ኢስላማዊ ሱናዎች) ናቸው፦ መገረዝ፣ የብልትን ፀጉር መላጨት፣ ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለን ፂም) ማሳጠር፣ ጥፍሮችን መቁረጥና የብብትን ፀጉር መንጨት ።
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands සිංහල தமிழ் ไทย دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली Malagasy Italiano or ಕನ್ನಡ Oromoo Română Soomaali Српски Wolof Українська Moore Azərbaycan ქართული Magyar mrالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመልክተኞች ሱናዎችና ከኢስላማዊ መገለጫዎች አምስቱን አብራሩ፦ የመጀመሪያው፦ መገረዝ ነው። እሱም ከወንድ ልጅ ብልት ከክርክሩ ከፍ ብሎ ያለውን ጭማሪ ቆዳና ከሴት ልጅ ብልት ደግሞ ከወንድ ብልት መግቢያ ስፍራ ከፍ ብሎ ያለውን ቆዳ ከጫፉ ቀንሶ መቁረጥ ነው። ሁለተኛው: የብልትን ፀጉር መቁረጥ ነው። ይህም ከብልት ዙሪያ ያለውን ፀጉር መላጨት ነው። ሶስተኛው: ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር: እሱም በወንድ ልጅ የላይኛው ከንፈር ላይ የበቀለን ፂም ከንፈሩ በግልፅ እስኪታይ መቁረጥ ነው። አራተኛው: ጥፍሮችን መቁረጥ ነው። አምስተኛው: የብብትን ፀጉር መንጨት ነው።فوائد الحديث
አላህ የሚወዳቸው፣ የሚቀበላቸውና ያዘዘባቸው የሆኑ የመልክተኞቹ ሱናዎች ወደ ምሉእነት፣ ንፅህናና ቁንጅና የሚጣሩ መሆናቸውን እንረዳለን።
እነዚህን ነገሮች ተጠባብቆ መፈፀም የተደነገገ መሆኑንና ከነዚህ ጉዳዮች አለመዘናጋት እንደሚገባ እንረዳለን።
እነዚህን ጉዳዮች በአግባቡ መፈፀም ዲናዊና አለማዊ ጥቅሞች አሉት። ከነሱም ውስጥ፦ አካልን ማስዋብ፣ ሰውነትን ማፅዳት፣ ለንፅህና ጥንቁቅ መሆን፣ ከሀዲያንን መቃረንና የአላህን ትእዛዝ መፈፀም ይገኝበታል።
በሌላ ሐዲሥ ውስጥ ከነዚህ አምስት ተፈጥሯዊ ሱናዎች ውጪ ያሉ ተጨማሪ ሱናዎች፤ ለምሳሌ: ፂምን መልቀቅ (ማፋፋት)፣ ሲዋክና ሌሎችም ተጠቅሰዋል።
التصنيفات
ተፈጥሯዊ ሱናዎች