አንዳችሁ የሚወደውን ህልም በተመለከተ ጊዜ እርሷ ከአላህ ናትና በርሷ ምክንያት አላህን ያመስግንም ለሌሎችም ያውራት፤ ከዚህ ውጪ የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ጊዜ ደሞ እርሷ ከሸይጧን…

አንዳችሁ የሚወደውን ህልም በተመለከተ ጊዜ እርሷ ከአላህ ናትና በርሷ ምክንያት አላህን ያመስግንም ለሌሎችም ያውራት፤ ከዚህ ውጪ የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ጊዜ ደሞ እርሷ ከሸይጧን ናትና ከክፋቷ በአላህ ይጠበቅ፤ ለአንድም ሰው አያውራ። እርሷም አትጎዳውም።

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ የአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቷል፦ "አንዳችሁ የሚወደውን ህልም በተመለከተ ጊዜ እርሷ ከአላህ ናትና በርሷ ምክንያት አላህን ያመስግንም ለሌሎችም ያውራት፤ ከዚህ ውጪ የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ጊዜ ደሞ እርሷ ከሸይጧን ናትና ከክፋቷ በአላህ ይጠበቅ፤ ለአንድም ሰው አያውራ። እርሷም አትጎዳውም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የሚያስደስት መልካም ህልም ማየት ከአላህ እንደሆነ ተናገሩ። በርሱም ላይ አላህን እንዲያመሰግንና ስለርሱም እንዲናገር ጠቆሙ። የሚጠላውንና የሚያሳዝነውን ህልም ያየ ጊዜ ደግሞ ከሸይጧን ነውና ከክፋቱ በአላህ እንዲጠበቅና ለአንድም ሰው እንዳያወራም ጠቆሙ። ህልምን ተከትሎ ከሚመጡ ጎጂ ነገሮች ሰላም ለመሆን ከላይ የተጠቀሰውን ማድረግ አላህ ሰበብ ስላደረገው ምንም አይጎዳውም።

فوائد الحديث

የህልም ክፍሎች: 1- መልካም ህልም: ይህም እውነተኛ የሆነ ህልምና ለሚያየው ወይም ለታየለት ሰው ከአላህ የሆነ ብስራት ነው። 2- በውስጡ ያወራው: ይህም ሰውዬው በነቃበት ወቅት ለነፍሱ ያወራው ነው። 3- ሸይጧን የአደም ልጆችን ለማሳዘን የሚያሳያቸው የሸይጣን ማሳዘኛ፣ ማስፈራሪያና ማስደንገጫ የሆነ ህልም ነው።

መልካም ህልም ባየ ሰው ዙሪያ የተጠቀሱት ነጥቦች ሶስት ናቸው: አላህን ማመስገን፣ በህልሙ መደሰትና ስላየው ህልም መናገር ናቸው። ነገር ግን የሚናገረው ለሚጠላው ሳይሆን ለሚወደው ሰው ብቻ ነው።

የሚጠላውን ህልም ባየ ሰው አደብ ዙሪያ የተጠቀሱ ነጥቦች አምስት ነገሮች ናቸው: ከህልሙ ክፋትና ከሸይጧን ክፋት በአላህ መጠበቅ፣ ከእንቅልፉ በሚነቃ ጊዜ ወደ ግራው ዞሮ ሶስት ጊዜ መትፋት፣ ከመሰረቱ ለማንም ሰው አለመንገር፣ ወደ መኝታው መመለስ ከፈለገ የነበረበትን ጎን ቀይሮ መዞር ነው። ህልሙም አይጎዳውም።

ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «መልካም ህልም ሲያይ ለማይወደው ሰው ያለመናገሩ ጥበብ መልካም ህልሙን ለማይወደው ሰው ሲናገር በጥላቻ ወይም በምቀኝነት ምክንያት በማያስደስተው ነገር ይፈታለትና በፈታለት መልኩም ሊከሰት ስለሚችል ነው። ወይም ያ የማይወደው ሰው በሰማው መልካም ህልም ትካዜና ብስጭቱ ሊቻኮልበት ስለሚችል ነው። ስለዚህም በዚህ ምክንያት ለማይወደው ሰው ማውራትን እንዲተው ታዘዘ።»

የአላህ ፀጋዎች በሚከሰቱና ችሮታዎች በሚታደሱ ወቅት ማመስገን እንደሚገባና ይህም እንዲዘወትር ማድረጊያ አንዱ ሰበብ መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

የህልም ስነ-ስርዓት