إعدادات العرض
ሰዎች በመክሰሳቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም (ለመውሰድ) ይከሱ ነበር። ነገር ግን ማስረጃ በከሳሽ ላይ፣ መሀላ ደግሞ ባወገዘ ሰው ላይ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው…
ሰዎች በመክሰሳቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም (ለመውሰድ) ይከሱ ነበር። ነገር ግን ማስረጃ በከሳሽ ላይ፣ መሀላ ደግሞ ባወገዘ ሰው ላይ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ተደረገ።
ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሰዎች በመክሰሳቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም (ለመውሰድ) ይከሱ ነበር። ነገር ግን ማስረጃ በከሳሽ ላይ፣ መሀላ ደግሞ ባወገዘ ሰው ላይ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ተደረገ።"
[ሶሒሕ ነው።] [Al-Bayhaqi]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Português සිංහල অসমীয়া Kiswahili Tagalog Tiếng Việt ગુજરાતી Nederlands پښتو नेपाली മലയാളം Svenska ไทย Кыргызча Română Malagasy ಕನ್ನಡ Српски తెలుగు فارسی ქართული Mooreالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰዎች ያለማስረጃና ያለ ጠቋሚ ማስረጃ በመክሰሳቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም ለመውሰድ ይከሱ እንደነበር፤ ነገር ግን ከሳሽ ለፈለገው ጉዳይ ማስረጃ የማስቀደም ግዴታ እንዳለበት ማስረጃ ከሌለው ደግሞ ክሱ ወደ ተከሳሽ ይቀርብና ክሱን ካወገዘው በመማል ራሱን ከጥፋተኝነት እንደሚያነፃ ገለፁ።فوائد الحديث
ኢብኑ ደቂቅ አልዒዲ እንዲህ ብለዋል: «ይህ ሐዲሥ ከህግጋቶች መሰረት መካከል አንዱ መሰረትና በንትርክና መካሰስ ወቅት የምንጠቀመው ትልቅ ምንጭ (መመለሻ) ነው።»
ሸሪዓ የሰዎችን ገንዘብና ደም ከመጫወቻነት ለመጠበቅ የመጣ እንደሆነ እንረዳለን።
ዳኛ በእውቀቱ አይፈርድም። ይልቁንም ፍርድ የሚመለሰው ወደ ማስረጃ ነው።
ማንኛውንም ሙግት የሞገተና ሙግቱ ከማስረጃ የፀዳ ከሆነ ተመላሽ ነው። ይህም በመብቶችም፣ በግብይይትም ይሁን በኢማንና እውቀት ዙሪያም የሚሰራ መርህ ነው።
التصنيفات
ሙግትና ማስረጃ