إعدادات العرض
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደኛ መጡ። እኛም እንዲህ ብለን ጠየቅናቸው የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርሶ ላይ እንዴት ሰላምታ…
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደኛ መጡ። እኛም እንዲህ ብለን ጠየቅናቸው የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርሶ ላይ እንዴት ሰላምታ እንደምናቀርብ አውቀናል። በርሶ ላይ ሶላት የምናወርደውስ እንዴት ነው?
ከዐብዱረሕማን ቢን አቢ ለይላ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ከዕብ ቢን ዑጅራህ አገኘኝና እንዲህ አለኝ: 'ስጦታ ላበርክትልህን? ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደኛ መጡ። እኛም እንዲህ ብለን ጠየቅናቸው የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርሶ ላይ እንዴት ሰላምታ እንደምናቀርብ አውቀናል። በርሶ ላይ ሶላት የምናወርደውስ እንዴት ነው? እርሳቸውም፦ ‹አልላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊ ሙሐመዲን ከማ ሶለይተ ዓላ አሊ ኢብራሂመ ኢነከ ሐሚዱን መጂድ፤ አልላሁመ ባሪክ ዓላ ሙሐመዲን ወዓላ አሊ ሙሐመዲን ከማ ባረክተ ዓላ አሊ ኢብራሂመ ኢነከ ሐሚዱን መጂድ። በሉ› አሉን።'" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ውዳሴህን ለኢብራሂምና ለቤተሰቦቻቸው እንዳወረድክላቸው ሁሉ ለሙሐመድና ለቤተሰቦቻቸው አውርድላቸው፤ አንተ ምስጉንና ኋያል (የላቅክ) ነህና፡፡አላህ ሆይ! ለኢብራሂምና ለቤተሰቦቻቸው ረድዔትን እንዳወረድክላቸው ሁሉ ለሙሐመድና ለቤተሰቦቻቸውም ረድዔትን አውርድላቸው፡፡ አንተ ምስጉንና ኋያል (የላቅክ) ነህና፡፡”)
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî සිංහල Русский Svenska ગુજરાતી Yorùbá Tiếng Việt Kiswahili پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Malagasy नेपाली Čeština Oromoo Română Nederlands Soomaali తెలుగు മലയാളം ไทย Српски Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Lietuvių Wolofالشرح
ሶሐቦች አትተሒያቱ ላይ "አስሰላሙ ዐለይከ አይዩሀ ነቢዩ ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱሁ… " በማለት በነቢዩ ላይ እንዴት ሰላምታ እንደሚቀርብ ካወቁ በኋላ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በርሳቸው ላይ ሶላት እንዴት እንደሚደረግ ጠየቁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በርሳቸው ላይ እንዴት ሶላት እንደሚያወርዱ ነገሯቸው። ትርጉሙም: "አልላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዲን ወዓላ አሊ ሙሐመድ" ማለትም: አላህ ሆይ! በላይኛው አለም፤ በርሳቸው፣ እምነታቸውን በተከተሉና አማኝ በሆኑ ቅርብ ዘመዶቻቸውም ላይ በመልካም ትውስታ አወድሳቸው። "ከማ ሶለይተ ዓላ አሊ ኢብራሂም" በኢብራሂም (ዐለይሂ ሰላም) የአላህ ሰላም ይስፈንባቸውና ቤተሰቦች ‐ እነሱም ኢብራሂም፣ ኢስማዒል፣ ኢስሐቅ፣ ዝርያዎቻቸውና አማኝ ተከታዮቻቸው ‐ ላይ ችሮታህን እንደዋልከው በሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይም ችሮታህን ዋል። "ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ" ማለትም: በዛትህ፣ በባህሪትህ እና በድርጊቶችህ ምስጉን የሆንክ፤ በልቅናህ፣ በስልጣንህና በስጦታህ ሰፊ የሆንክ አንተው ነህ ማለት ነው። "አልላሁመ ባሪክ ዐላ ሙሐመዲን ወዓላ አሊ መሐመድ ከማ ባረክተ ዓላ አሊ ኢብራሂም" ማለትም ለነቢዩ ከመልካሙና ከክብር የላቀውን ስጣቸው፣ ጨምርላቸውም፣ አፅናላቸውም።فوائد الحديث
ቀደምት አበው እውቀታዊ ቁምነገሮችን እንደ ስጦታ ይሰጣጡ እንደነበር እንረዳለን።
ሶላት ላይ በመጨረሻው ተሸሁድ ወቅት በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ሶላት ማውረድ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባልደረቦቻቸውን በርሳቸው ላይ እንዴት ሶላትና ሰላም እንደሚያወርዱ ማስተማራቸውን እንረዳለን።
ይህ የሶለዋት ይዘት በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ የተሟላው የሶለዋት ይዘት ነው።