ያለ ወሊይ ፈቃድ ጋብቻ የለም።

ያለ ወሊይ ፈቃድ ጋብቻ የለም።

ከአቡ ሙሳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦ "ያለ ወሊይ ፈቃድ ጋብቻ የለም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዲት ሴት የጋብቻዋን ውል ለማሰር ሀላፊነት በሚወስድ ወሊይ ካልሆነ በስተቀር ጋብቻ መፈፀም እንደማይበቃላት ገለፁ።

فوائد الحديث

የወሊይ መኖር ጋብቻው ትክክለኛ እንዲሆን መስፈርት ነው። ያለ ወሊይ ወይም ሴቲቱ ራሷን ብትድር ጋብቻው አይበቃም።

ወሊይ የሚሆነው ወደ ሴቷ እጅግ ቅርብ ዘመድ የሆነ ወንድ ነው። ከርሱ የቀረበ ወሊይ እያለ ሩቅ የሆነ ወሊይ እሷን ማጋባት አይችልም።

ወሊይ ለመሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይገባዋል: - አቅመ አዳምና የአይምሮ ጤነኛ (ሙከለፍ) መሆን፣ ወንድ መሆን፣ የጋብቻን ጥቅም የሚያውቅ አስተዋይ መሆኑ (ቂላቂል አለመሆን) ፣ ወሊዩና ተጋቢዋ ተመሳሳይ እምነት መከተላቸው ነው። እነዚህን ባህሪያቶች ያልተላበሰ የጋብቻን ውል በማሰር ረገድ ለወሊይነት የተገባ አይደለም።

التصنيفات

ጋብቻ