إعدادات العرض
አስካሪ ሁሉ ኸምር ነው። አስካሪ ሁሉ ክልክል ነው። በዚህ ዓለም አስካሪ መጠጥ አዘውትሮ ጠጥቶ ንስሀ ሳይገባ የሞተ ሰው በመጪው ዓለም አይጠጣም።
አስካሪ ሁሉ ኸምር ነው። አስካሪ ሁሉ ክልክል ነው። በዚህ ዓለም አስካሪ መጠጥ አዘውትሮ ጠጥቶ ንስሀ ሳይገባ የሞተ ሰው በመጪው ዓለም አይጠጣም።
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አስካሪ ሁሉ ኸምር ነው። አስካሪ ሁሉ ክልክል ነው። በዚህ ዓለም አስካሪ መጠጥ አዘውትሮ ጠጥቶ ንስሀ ሳይገባ የሞተ ሰው በመጪው ዓለም አይጠጣም።"»
[ሶሒሕ ነው።]
الترجمة
العربية Bosanski English فارسی Français Русский हिन्दी 中文 ئۇيغۇرچە Bahasa Indonesia اردو Kurdî Português دری অসমীয়া Tiếng Việt Svenska ไทย Yorùbá Кыргызча Kiswahili ગુજરાતી Hausa नेपाली Română മലയാളം Nederlands Oromoo සිංහල پښتو తెలుగు Lietuvių Kinyarwanda Malagasy Türkçe ಕನ್ನಡالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አይምሮን የሚያደነዝዝና የሚያስወግድ የሚጠጣም ይሁን የሚበላም ይሁን የሚሸተት ወይም ከዚህ ውጪ ያለ ነገር ሁሉ ኸምርና አስካሪ መሆኑን ገለፁ። ሁሉም አስካሪና አይምሮን የሚያስወግድ ነገርም አነሰም በዛም አላህ ከልክሎታል። ከነዚህ የአስካሪ አይነቶች መካከል ማንኛውንም አይነት የወሰደና በመውሰድ ላይም የዘወተረ እስኪሞት ድረስም ንስሀ ያልገባ ሰውም ጀነት ውስጥ መጠጣትን በመነፈግ የአላህ ቅጣት ይገባዋል።فوائد الحديث
የኸምር ክልክልነት ምክንያቱ ማስከሩ ነው። ስለዚህ ማንኛውም አይነት አስካሪ ክልክል ነው።
አላህ አስካሪ መጠጥን የከለከለው ትላልቅ ጉዳትና ብልሽቶችን ስለያዘ ነው።
ኸምርን ጀነት ውስጥ ሲሆን መጠጣቱ የድሎትና የእርካታ ማሟያ ነው።
በዚህ አለም አስካሪ መጠጥ ከመጠጣት ነፍሱን ያላቀበ አላህ ጀነት ውስጥ ከመጠጣት ይከለክለዋል። ምንዳ የሚሆነው በሰራው ስራ አይነት ነውና።
ከሞት በፊት ከወንጀሎች ንስሀ በማድረግ ላይ መቻኮል እንደሚገባ መነሳሳቱን እንረዳለን።
التصنيفات
የተከለከሉ መጠጦች