'ሱረቱል ኢኽላስ እና ሁለቱን መጠበቂያዎች (ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱን-ናስን) ስታመሽና ስታነጋ ሶስት ጊዜ ካልክ ለሁሉም ነገር ይበቁሃል።' አሉኝ።

'ሱረቱል ኢኽላስ እና ሁለቱን መጠበቂያዎች (ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱን-ናስን) ስታመሽና ስታነጋ ሶስት ጊዜ ካልክ ለሁሉም ነገር ይበቁሃል።' አሉኝ።

ከዐብደላህ ቢን ኹበይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "በዝናባማና በድቅድቅ ጨለማ ምሽት የአላህ መልክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኛን እንዲያሰግዱን ፈልገን ወጣን። አገኘኋቸውና 'በል!' አሉኝ። ምንም አላልኩኝም። ቀጥለውም 'በል!' አሉኝ። ምንም አላልኩኝም። አሁንም 'በል!' አሉኝ። እኔም ምን ልበል? አልኳቸው። እርሳቸውም 'ሱረቱል ኢኽላስ እና ሁለቱን መጠበቂያዎች (ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱን-ናስን) ስታመሽና ስታነጋ ሶስት ጊዜ ካልክ ለሁሉም ነገር ይበቁሃል።' አሉኝ።"

[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።]

الشرح

ታላቁ ሶሐባ ዐብደላህ ቢን ኹበይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና በርካታ ዝናብ በሚዘንብበትና ድቅድቅ ጨለማ በነበረበት ምሽት የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲያሰግዷቸው ፈልገው እንደወጡና እንዳገኟቸው ተናገረ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ "በል!" ማለትም አንብብ! አሉት። እርሱም ምንም አላነበበም። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ንግግራቸውን ሲደጋግሙለት ዐብደላህም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ልቅራ?" አላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ሱረቱል ኢኽላስን እና ሁለቱን መጠበቂያዎች ሱረቱል ፈለቅ እና ሱረቱ አን-ናስን በምሽት ወቅትና በንጋት ወቅት ሶስት ጊዜ ቅራ! ከሁሉም ክፋትና ጉዳት ይጠብቅሃል።" አሉት።

فوائد الحديث

ከሁሉም ክፋት መጠበቂያ ስለሆኑ ንጋትና ምሽት ላይ ሱረቱል ኢኽላስንና ሁለቱን መጠበቂያዎች መቅራት ይወደዳል።

የሱረቱል ኢኽላስንና ሁለቱ መጠበቂያዎችን መቅራት ትሩፋት እንረዳለን።

التصنيفات

የንጋትና ምሽት ዚክሮች