إعدادات العرض
ሆነ ብሎ በኔ ላይ የዋሸ ሰው ከእሳት የሆነ መቀመጫውን ያዘጋጅ።
ሆነ ብሎ በኔ ላይ የዋሸ ሰው ከእሳት የሆነ መቀመጫውን ያዘጋጅ።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሆነ ብሎ በኔ ላይ የዋሸ ሰው ከእሳት የሆነ መቀመጫውን ያዘጋጅ።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە සිංහල हिन्दी Hausa Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Türkçe Tiếng Việt नेपाली Malagasy Kinyarwanda తెలుగు Bosanski Lietuvių Oromoo Română മലയാളം Nederlands Soomaali Српски Kurdî Українська Deutsch ಕನ್ನಡ Wolof Moore Shqip Português ქართული Azərbaycan 中文 Magyar فارسیالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሆን ብሎ ንግግርን ወይም ድርጊትን ወደርሳቸው አስጠግቶ በርሳቸው ላይ የዋሸ ሰው በመጨረሻው ዓለም በርሳቸው ላይ ለመዋሸቱ ምንዳ የእሳት መቀመጫ እንዳለው ገለፁ።فوائد الحديث
በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ አውቆና ሆን ብሎ መዋሸት እሳት ለመግባት ምክንያት እንደሆነ እንረዳለን።
በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ መዋሸትን ተከትሎ ከሚመጣው ዱንያዊና ሃይማኖታዊ ብልሽት ከባድነት አንፃር እርሳቸው ላይ መዋሸት በሌሎች ሰዎች ላይ እንደመዋሸት እንዳልሆነ እንረዳለን።
ሐዲሦች በትክክል ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መነገራቸውን ሳናረጋግግጥ በፊት ማሰራጨት መከልከሉን እንረዳለን።