إعدادات العرض
እናንተ ሰዎች ሆይ! ይህንን የፈፀምኩት በኔ እንድትከተሉና አሰጋገዴንም እንድታውቁ ነው።'
እናንተ ሰዎች ሆይ! ይህንን የፈፀምኩት በኔ እንድትከተሉና አሰጋገዴንም እንድታውቁ ነው።'
ከአቡ ሐዚም ቢን ዲናር እንደተዘገበው: የተወሰኑ ሰዎች የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሚንበር ከምን አይነት እንጨት ነው የተሰራው? በሚለው ተከራክረው ሰህል ቢን ሰዕድ አስሳዒዲይ ዘንድ መጡ። ስለጉዳዩም ጠየቁት። እርሱም "ወላሂ እኔ ከምን እንደተሰራ አውቃለሁ። መጀመሪያ የተኖረበት ቀንና የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በርሱ ላይ መጀመሪያ የተቀመጡ እለት ተመልክቼዋለሁ። የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ እከሊት (ከአንሷር የሆነች ሴት ስትሆን ሰህል ስሟን ጠርቷት ነበር።) "አናጢውን አገልጋይሽን ለሰዎች ንግግር ሳደርግ የምቀመጥበትን እንጨት እንዲሰራልኝ እዘዢ።" በማለት መልእክት ላኩላት። እርሷም አዘዘችው። እርሱም ሚንበሩን ‹ጦርፋኡል ጛባ› (ጠደቻ) ከሚባለው የእንጨት አይነት ሰርቶ ወደርሷ አመጣ። እርሷም ወደ አላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላከችው። በርሳቸው ትእዛዝም እዚህ ጋር ተቀመጠ። ከዚያም የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እርሱ ላይ ሲሰግዱበት ተመልክቻቸዋለሁ። ሚንበሩ ላይ እንዳሉ ተክቢራ አደረጉ ፣ እዛው ላይ እያሉም ሩኩዕ አደረጉ፣ ከዚያም ወደኋላ ወረዱ፣ ከሚንበሩ ስር ሱጁድ አደረጉና እንደገና ወደ ሚንበሩ ተመለሱ። ሶላቱን ያጠናቀቁ ጊዜ ወደ ሰዎች በመዞር እንዲህ አሉ 'እናንተ ሰዎች ሆይ! ይህንን የፈፀምኩት በኔ እንድትከተሉና አሰጋገዴንም እንድታውቁ ነው።'"
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली മലയാളം తెలుగు Bosanski Italiano ಕನ್ನಡ Kurdî Oromoo Română Soomaali Shqip Српски Українська Wolof Moore Tagalog O‘zbek Malagasy தமிழ் Azərbaycan فارسی ქართული 中文 Magyarالشرح
የተወሰኑ ሰዎች ወደ አንድ ሶሐባ የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ንግግር ሲያደርጉ የሚጠቀሙበት ሚንበር ከምን እንደተሰራ ሊጠይቁት መጡ። በዚህ ዙሪያም አየተነታረኩና እየተከራከሩ ነበር። ሱሓቢዩም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አናጢ አገልጋይ ወደነበራት የአንሷር ሴት "ለሰዎች ንግግር በማደርግበት ወቅት የምቀመጥበትን ሚንበር ለኔ እንዲሰራልኝ አገልጋይሽን እዘዢልኝ።" በማለት መልዕክተኛ መላካቸውን፤ እርሷም ትእዛዛቸውን በመቀበል አገልጋዩዋን ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጦርፋእ ዛፍ ሚንበር እንዲሰራ ማዘዟን፤ ያጠናቀቀ ጊዜም ሚንበሩን ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መላኳን እርሳቸውም መስጂድ ውስጥ ቦታው ላይ እንዲቀመጥ አዘው መቀመጡንና ሚንበሩ ላይም መስገዳቸውን አወሳ። ሚንበሩ ላይ ሆነው ተክቢራ አደረጉ፣ እርሱ ላይ እንዳሉም ሩኩዕ አደረጉ፣ ከዚያም ፊታቸውን ወደኋላ አቅጣጫ ሳያዞሩ ወደኋላ እያፈገፈጉ በመውረድ ሚንበሩ ስር ሱጁድ ወረዱ፣ ከዚያም ወደ ሚንበሩ ተመለሱ። በዚህ መልኩ ሰግደው እንዳጠናቀቁም ወደ ሰዎች በመዞር እንዲህ አሉ: "እናንተ ሰዎች ሆይ! ይህንን የፈፀምኩት እንድትከተሉኙና አሰጋገዴን እንድታውቁ ነው።"فوائد الحديث
ሚንበርን ማዘጋጀትና ኹጥባ አድራጊ እርሱ ላይ መውጣቱ እንደሚወደድ እንረዳለን። ጥቅሙም ድምፅን ማዳረስና ማሰማት ነው።
በማስተማር አላማ ሚንበር ላይ መስገድ እንደሚፈቀድና አስፈላጊ ከሆነ ኢማሙ ከተከታዮቹ ከፍ ማለቱም እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
ለሙስሊሞች ጥቅም ሲባል በሙያተኞች መታገዝ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
አስፈላጊ ከሆነ ሶላት ውስጥ ትንሽ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
ሶላት ውስጥ ተከታይ የሆነ ሰው ከኢማሙ ለመማር በሚል ወደ ኢማሙ መመልከቱ እንደሚፈቀድና ይህም በተመስጦ ከመስገድ ጋር እንደማይፃረር እንረዳለን።
التصنيفات
የሶላት አሰጋገድ