إعدادات العرض
የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሩኩዕ ወገባቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜ "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ
የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሩኩዕ ወገባቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜ "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ
ከኢብኑ አቢ አውፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሩኩዕ ወገባቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜ "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ አላሁመ ረበና ለከል ሐምዱ ሚልአስ-ሰማዋቲ ወልአርድ ወሚልአ ማ ሺእተ ሚን ሸይኢን በዕዱ" ይሉ ነበር። ትርጉሙም "አላህ ላመሰገነው ሰው ሰሚ ነው። አላህ ሆይ! ሰማያትን የሞላ፣ ምድርን የሞላ፣ ከነዚህም በኋላ ያሉ የፈለግከውን ነገሮችን የሞላ ምስጋና ላንተ የተገባ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली తెలుగు Bosanski ಕನ್ನಡ Kurdî മലയാളം Oromoo Română Italiano Soomaali Shqip Српски Українська Wolof Moore Português Tagalog Malagasy தமிழ் Azərbaycan فارسی ქართული 中文 Magyarالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ውስጥ ከሩኩዕ ወገባቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜ "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" ይሉ ነበር። አላህን ያመሰገነ ሰው አላህ ይቀበለዋል፤ ምስጋናውን ተቀብሎ ይመነዳዋል ማለት ነው። ከዚያም "አላሁመ ረበና ለከል ሐምዱ ሚልአስ-ሰማዋቲ ወልአርድ ወሚልአ ማ ሺእተ ሚን ሸይኢን በዕዱ" በሚለው ንግግራቸው ሰማያትን፣ ምድሮችን፣ በመካከላቸው ያለውን፣ አላህ የሻውን ነገርንም ሁሉ በሚሞላ ምስጋና አላህን ያመሰግናል።فوائد الحديث
ሰጋጅ የሆነ ሰው ራሱን ከሩኩዕ ቀና ያደረገ ጊዜ ማለቱ የሚወደድለት ዚክር መገለፁ።
ከሩኩዕ ከተነሳ በኋላ መረጋጋትና ቀጥ ማለት መደንገጉን እንረዳለን። ምክንያቱም ይህን ዚክር ቀጥ ብሎና ተረጋግቶ ካልሆነ በቀር ማለቱም አይመችምና።
በሁሉም ሶላቶች ግዴታም ሆነ ሱና ሶላት ይህንኑ ዚክር ማለቱ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።