إعدادات العرض
እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ ከቆጠርኩና (ከተቀበልኩ)
እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ ከቆጠርኩና (ከተቀበልኩ)
ከአቡ ዓብደላህ ጃቢር ቢን ዐብደላህ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው: «አንድ ሰውዬ የአላህን መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡- “ እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ ከቆጠርኩና (ከተቀበልኩ) በዛም ላይ ምንም ካልጨመርኩ ጀነት እገባለሁን?” ነቢዩም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - “አዎን!” አሉት።»
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Español English اردو Indonesia বাংলা Français Türkçe Русский Bosanski සිංහල हिन्दी 中文 فارسی Tiếng Việt Tagalog Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ ไทย Deutsch پښتو অসমীয়া Shqip Nederlands ગુજરાતી Кыргызча नेपाली Lietuvių دری Српски тоҷикӣ Kinyarwanda Română Magyar Čeština Moore Malagasy Oromoo ಕನ್ನಡ Wolof Azərbaycan O‘zbek Українська ქართული Македонски ភាសាខ្មែរ Bambara ਪੰਜਾਬੀ मराठी Kirundi Kurmancî Bahasa Melayuالشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አምስቱን ግዴታ ሰላቶች የሰገደና አንድም ተጨማሪ ሰላት ጨምሮ ያልሰገደ ፣ ረመዳንን የፆመና ከዚህም ሱና ፆሞችን ያልጨመረ፣ (ሐላል) ፍቁድ ነገሮችን በፍቁድነታቸው አምኖ የተገበረና ሐራም ነገሮችን በክልክልነታቸው አምኖ የራቀ ጀነት እንደሚገባ ይገልጻሉ።فوائد الحديث
አንድ ሙስሊም መጨረሻው ጀነት መግባት እንዲሆን፥ ግዴታዎችን በመተግበር እና ክልከላን በመተው ላይ ጥረት ሊኖረው ይገባል ።
ሐላል ፍቁድ ነገሮችን ፍቁድነታቸውን በማመን መተግበርና ክልክል ነገሮችን ክልክልነታቸውን በማመን መራቅ አሳሳቢ (ወሳኝ) ጉዳይ መሆኑን ፤
ግዴታዎችን መፈፀምና ክልክሎችን መተው ጀነት መግቢያ (ሰበብ) ምክንያት ነው።
