إعدادات العرض
ፆም
ፆም
1- (ግዴታነቱን) አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አስቦ የረመዳንን ወር የፆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።
2- መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።
4- አላህ እንዲህ ብሏል: ‹ሁሉም የአደም ልጅ ስራ ለርሱ ነው ፆም ሲቀር፤ ፆም ለኔ ነው። በርሱ የምመነዳውም እኔው ነኝ።
7- ጨረቃን ባያችሁ ጊዜ ፁሙ! ባያችሁት ጊዜ ፆም ፍቱ! ከተጋረደባችሁ ደሞ ልኩን ገምቱለት።
10- እኔ የበኑ ሰዕድ ቢን በክር ወንድም ዲማም ቢን ሠዕለባህ ነኝ።" አላቸው።
13- በአላህ መንገድ ላይ አንድ ቀን የጾመ ሰው አላህ ፊቱን ከእሳት ሰባ ዓመታት ያርቀዋል።
14- ሰዎች ማፍጠርን እስካቻኮሉ ድረስ መልካም ላይ ከመሆን አይወገዱም።
17- ሰሑር ተመገቡ! በሰሑር ውስጥ በረከት አለ።
18- ከረመዷን አንድ ቀንም ሆነ ሁለት ቀን በፊት ቀድማቹህ አትፁሙ። ነገር ግን ያስለመደው ጾም የነበረበት ሰው ከሆነ ይፁመው።
19- ጾመኛ መሆኑን ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙን ይሙላ። ያበላውና ያጠጣው አላህ ነውና።
21- ለይለቱል ቀድርን በረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናቶች በጎደሎ ቁጥሮቹ ውስጥ ፈልጓት።
24- አመቱን ሙሉ የጾመ አልጾመም። በወር ሶስት ቀን መጾም አመቱን ሙሉ እንደመጾም ነው።
25- ረመዳን የገባ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የእሳት በሮችም ይዘጋሉ፤ ሰይጣኖችም ይጠፈነጋሉ።
