إعدادات العرض
መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።
መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው - እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە සිංහල ไทย دری Fulfulde Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy or Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ O‘zbek Moore नेपाली Oromoo Wolof Soomaali Български Українська Azərbaycan bm ქართული Lingala Македонскиالشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በረመዳን ከመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ የምትገኘው መወሰኛይቱ ሌሊትን (ለይለቱል ቀድርን) የመቆም ትሩፋትን ተናገሩ። በዚህች ሌሊት በሷና ስለሷ ትሩፋት በመጡ ሐዲሦች አምኖ እንዲሁም በስራው ይዩልኝና ይስሙልኝን ሳይሆን የአላህን ምንዳ ከጅሎ በሶላት፣ በዱዓእ፣ ቁርአን በመቅራትና በዚክር የታገለ ሰው ያለፈውን ኃጢዓቱ ይማራል።فوائد الحديث
የመወሰኛይቱ ሌሊት (የለይለቱል ቀድር) ትሩፋትና ይህቺን ሌሊት መቆም ላይ የሚበረታታ መሆኑ፤
መልካም ስራዎች ከእውነተኛ ኒያ ጋር ካልሆነ በቀር ተቀባይነት አያገኙም።
የመወሰኛይቱ ሌሊትን (የለይለቱል ቀድርን) አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ለሱ መማሩ የአላህን እዝነትና ትሩፋት እንረዳበታለን።