የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የሴት ልጅ አለባበስን የሚለብስን ወንድና የወንድ ልጅ አለባበስን የምትለብስ ሴትን ረገሙ።

የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የሴት ልጅ አለባበስን የሚለብስን ወንድና የወንድ ልጅ አለባበስን የምትለብስ ሴትን ረገሙ።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የሴት ልጅ አለባበስን የሚለብስን ወንድና የወንድ ልጅ አለባበስን የምትለብስ ሴትን ረገሙ።"

[ሶሒሕ ነው።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በአኳኋኑም ይሁን በቀለሙም፣ በአይነቱም ይሁን በአለባበስ መንገዱም፣ በመዋቢያነቱ (ማስጌጫዎች)ና በመሳሰሉ መንገዶች ሴት ልጅ የተለየችበት በሆነ ልብስ የሚመሳሰል ወንድ ላይ ከአላህ እዝነት እንዲባረርና እንዲርቅ ዱዓእ አድርገዋል። ወይም ልክ እንደዚሁ ወንድ ልጅ በተለየበት ልብስ የምትመሳሰል ሴት ልጅ ከአላህ እዝነት እንዲባረሩና እንዲርቁ ዱዓ አደረጉ። ይህም ከትላልቅ ወንጀሎች የሚመደብ ከባድ ወንጀል ነው።

فوائد الحديث

ሸውካኒይ እንዲህ ብለዋል: "ሴት ልጅ ከወንድ ልጅ ጋር መመሳሰሏ፣ ወንዶችም ከሴት ጋር መመሳሰላቸው መከልከሉን እንረዳለን። ምክንያቱም እርግማን ክልክል ተግባርን በመፈፀም ካልሆነ በቀር አይሆንምና ነው።"

ኢብኑ ዑሠይሚን እንዲህ ብለዋል: "ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የሚለብሱት የሆኑ አንዳንድ ልብሶችን ለምሳሌ ሁለቱም በጋራ የሚለብሷቸው ቲሸርቶችን መልበስ ችግር የለውም። ማለትም ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የሚለብሱት የጋራ ልብስ ስለሆነ መልበሱ ችግር የለውም።"

التصنيفات

የተከለከለው መመሳሰል, ልብስና ጌጥ