አንድ አማኝ ወንድ አንዲትን አማኝ እንስት አይጥላ። ከርሷ አንድ ባህሪዋን ቢጠላ እንኳ ሌላ የሚወደው ባህሪ አላትና።

አንድ አማኝ ወንድ አንዲትን አማኝ እንስት አይጥላ። ከርሷ አንድ ባህሪዋን ቢጠላ እንኳ ሌላ የሚወደው ባህሪ አላትና።

ከአቡ ሁረይራ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንድ አማኝ ወንድ አንዲትን አማኝ እንስት አይጥላ። ከርሷ አንድ ባህሪዋን ቢጠላ እንኳ ሌላ የሚወደው ባህሪ አላትና።" ወይም "ከርሱ ውጪ ያለን ባህሪ… " ብለዋል።

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባል ሚስቱን ወደ መበደል፣ ወደ መተውና ችላ ወደማለት የሚያደርስ የሆነ ጥላቻን ከመጥላት ከለከሉ። የሰው ልጅ በጉድለት ላይ የተፈጠረ ነው። በሚስቱ ላይ መጥፎ ባህሪዋን ቢጠላ እንኳ ሌላ መልካም ባህሪን እርሷ ላይ ያገኛል። ከርሱ ጋር የሚስማማውን መልካም ባህሪ ይውደድላትና የማይወድላትን መጥፎ ባህሪ ደግሞ ይታገስ። ይህም እንዲታገስ የሚያደርገውና ወደመለያየት የሚያደርስ ጥላቻን ከመጥላት የሚታደግ ነው።

فوائد الحديث

ሙእሚን ከሚስቱ ጋር በሚከሰት ማንኛውም ዓይነት አለመግባባት ላይ ወደ ፍትህ እና ህሊናን ወደ ማስዳኘት (ምክንያታዊነት) እንጂ ስሜትን እና ግንፍልተኝነትን ወደ ማስዳኘት መሄድ እንደሌለበት እንረዳለን።

የሙእሚን ጉዳይ ከአማኝ ሚስቱ ጋር ወደ መለያየት በሚገፋፋው መልኩ ሙሉ በሙሉ መጥላት ሳይሆን የጠላውን በወደደው ነገር ማካካስ ነው የሚገባው።

በትዳር ጥንዶች መካከል በመልካም መኗኗርና መጎዳኘት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

ኢማን ወደ መልካም ስነ ምግባር ይጣራል። ማንኛውም ወንድ ወይም ሴት አማኝ መልካም ስነምግባር ላይ ከመሆን አይወገድም። ኢማን በውስጣቸው የተመሰገኑ ባሕርያት እንዲኖራቸው ያስገድዳልና።

التصنيفات

ጋብቻ, የሴቶች ህግጋት