ባሮች የሚያነጉበት አንድም ቀን የለም ሁለት መልዐክ ወርደው እንዲህ የሚሉበት ቢሆን እንጂ፤ አንደኛቸው: "አላህ ሆይ! ለሰጪ ምትኩን ስጠው!" ሲል ሌላኛቸው ደግሞ "አላህ ሆይ! ለቋጣሪ…

ባሮች የሚያነጉበት አንድም ቀን የለም ሁለት መልዐክ ወርደው እንዲህ የሚሉበት ቢሆን እንጂ፤ አንደኛቸው: "አላህ ሆይ! ለሰጪ ምትኩን ስጠው!" ሲል ሌላኛቸው ደግሞ "አላህ ሆይ! ለቋጣሪ ጥፋትን ስጠው!" ይላል።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: «ባሮች የሚያነጉበት አንድም ቀን የለም ሁለት መልዐክ ወርደው እንዲህ የሚሉበት ቢሆን እንጂ፤ አንደኛቸው: "አላህ ሆይ! ለሰጪ ምትኩን ስጠው!" ሲል ሌላኛቸው ደግሞ "አላህ ሆይ! ለቋጣሪ ጥፋትን ስጠው!" ይላል።»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ፀሐይ በምትወጣበት ቀናት ሁሉ ሁለት መልአኮች ወርደው እንደሚጣሩ ተናገሩ። አንደኛቸው እንዲህ ይላል: አላህ ሆይ! አላህን ለመታዘዝ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለእንግዶቹ፣ ለበጎ አድራጎት ለሚሰጥ ሰው ምትኩን ስጠው፤ ካወጠው የተሻለ ተካለትም ባርክለትም። ሌላኛው ደግሞ "አላህ ሆይ! ከመስጠት የሚቋጥርን ጥፋትን ስጠው፤ ለሚገባቸው ከመስጠት ገንዘቡን የነፈገንም ገንዘቡን አውድምበት!" ይላል።

فوائد الحديث

ቸር ለሆነ ሰው ካወጣው የበዛ፣ ከሰጠው በተሻለ እንዲተካለት ዱዓ ማድረግ እንደሚፈቀድ፤ በስስታም ላይ ደግሞ የሰሰተበት ገንዘብና አላህ ግዴታ ባደረገበት ነገር ላይ ወጪ ከማድረግ የነፈገው ገንዘቡ እንዲጠፋ ዱዓ ማድረግ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።

መላዕክቶች ለደጋግና ሰጪ ለሆኑ አማኞች በመልካምና በበረከት ዱዓ እንደሚያደርጉላቸው እንረዳለን። የነርሱ ዱዓም ተቀባይነት ያለው ነው።

ለቤተሰብ፣ ዝምድና ለመቀጠልና ለተለያዩ በጎ አድራጎቶች በበጎ ፍቃደኝነትና ግዴታን በመወጣት ወጪ በማድረግ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

በመልካም ጉዳዮች ላይ ወጪ የሚያደርግ ሰው የሚያገኘው ትሩፋት መገለፁን እንረዳለን። ውጤቱም አላህ ባወጣው የሚተካለት መሆኑ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል: {ከማንኛውም ነገር የምትለግሱትን እርሱ ይተካዋል። እርሱም ከሲሳይ ሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው።} [ሰበእ: 39]

ይህ ዱዓ ከግዴታ ምፅዋቶች ንፉግ የሆነን ነው የሚመለከተው። ተወዳጅ ከሆኑ ምፅዋቶች ንፉግ የሆነ ሰው ባለቤቱ ይህ ዱዓ ስለማይገባው እዚህ ዱዓ ውስጥ አይገባም።

ንፉግነትና ስስታምነት ክልክል መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

የፈቃደኝነት ምፅዋት (ሶደቃ)