ልጆቻችሁን ሰባት አመት ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፤ አስር አመት ሲሞላቸው ሶላት ላለመስገዳቸው ምቷቸው፤ በመካከላቸውም የመኝታ ስፍራቸውን ለዩ!

ልጆቻችሁን ሰባት አመት ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፤ አስር አመት ሲሞላቸው ሶላት ላለመስገዳቸው ምቷቸው፤ በመካከላቸውም የመኝታ ስፍራቸውን ለዩ!

ዐምር ቢን ሹዐይብ ከአባቱና ከአያቱ እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "ልጆቻችሁን ሰባት አመት ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፤ አስር አመት ሲሞላቸው ሶላት ላለመስገዳቸው ምቷቸው፤ በመካከላቸውም የመኝታ ስፍራቸውን ለዩ!"

[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አባት ወንድና ሴት ልጆቹን ገና ሰባት ዓመት እያሉ ሶላት እንዲሰግዱ ማዘዝና ሶላትን በማስተካከል ላይ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ማስተማር እንዳለበት ገለፁ። አስር ዓመት የደረሱ ጊዜም ትእዛዙን ይጨምራል። ሶላትን በማጓደላቸው ይመታቸዋልም፤ በመኝታ ስፍራም በመካከላቸውም ይለያያቸዋል።

فوائد الحديث

ህፃናት ልጆችን አቅመ አዳም ከመድረሳቸውም በፊት የዲን ጉዳዮችን ማስተማር እንደሚገባ እንረዳለን። ከአንገብጋቢዎቹ መካከልም አንዱ ሶላት ነው።

መምታቱ ለሥርዓት (ለማስተማር) እንጂ ለመቅጣት አይደለምና ሁኔታውን በሚመጥን መልኩ መቅጣት ይገባል።

ሸሪዓ ክብርን ለመጠበቅ የሰጠውን ትኩረትና ወደ ብክለት የሚያደርስን መንገድ ሁሉ መዝጋቱን እንረዳለን።

التصنيفات

የሶላት ግዴታነትና የተወው ሰው ፍርድ