ምፅዋት (ከሰጪው) ገንዘብ ላይ አታጎድልም፤ አላህ ለአንድ ባሪያ ይቅር በማለቱ (ምክንያት) ከልቅና በስተቀር አይጨምርለትም፤ አንድም ሰው ለአላህ ብሎ አይተናነስም አላህ ከፍ ያደረገው…

ምፅዋት (ከሰጪው) ገንዘብ ላይ አታጎድልም፤ አላህ ለአንድ ባሪያ ይቅር በማለቱ (ምክንያት) ከልቅና በስተቀር አይጨምርለትም፤ አንድም ሰው ለአላህ ብሎ አይተናነስም አላህ ከፍ ያደረገው ቢሆን እንጂ።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል:- "ምፅዋት (ከሰጪው) ገንዘብ ላይ አታጎድልም፤ አላህ ለአንድ ባሪያ ይቅር በማለቱ (ምክንያት) ከልቅና በስተቀር አይጨምርለትም፤ አንድም ሰው ለአላህ ብሎ አይተናነስም አላህ ከፍ ያደረገው ቢሆን እንጂ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ምፅዋት ከሰጪው ላይ መከራን ትከላከላለች እንጂ ገንዘቡን እንደማታጎድል፤ አላህ ለሰጪው ትልቅ መልካምን እንደሚተካለትና መመፅወቱ ጭማሪ እንጂ ጉድለት እንደማይሆን ገለፁ። መበቀል ወይም ባለቤቱን መቅጣት እየተቻለም ይቅር ማለት ኃይልና ልቅናን እንጂ አይጨምርም። አንድም ሰው ማንንም ፈርቶ፣ ለማስመሰልና ከሱ ጥቅም ፈልጎ ሳይሆን ለአላህ ፊት ብሎ አይተናነስምም ዝቅ አይልምም ምንዳው ልቅናና ከፍታ ቢሆን እንጂ።

فوائد الحديث

አንዳንድ ሰዎች ከዚህ ተቃራኒ ቢያስቡም መልካምና ስኬት የሚገኘው ሸሪዐን በመተግበርና መልካምን በመፈፀም ነው።

التصنيفات

የፈቃደኝነት ምፅዋት (ሶደቃ)