إعدادات العرض
አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው ምርጡ?' ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም 'ምግብ መመገብህ፣ ሰላምታን ባወቅከውም ባላወቅከውም…
አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው ምርጡ?' ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም 'ምግብ መመገብህ፣ ሰላምታን ባወቅከውም ባላወቅከውም ሰው ላይ ማቅረብህ ነው።' ብለው መለሱለት።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:- "አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው ምርጡ?' ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም 'ምግብ መመገብህ፣ ሰላምታን ባወቅከውም ባላወቅከውም ሰው ላይ ማቅረብህ ነው።' ብለው መለሱለት።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt Hausa Kurdî Português සිංහල Svenska ગુજરાતી Yorùbá ئۇيغۇرچە Kiswahili پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Malagasy नेपाली Čeština Oromoo Română Nederlands Soomaali తెలుగు ไทย മലയാളം Српски Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Lietuvių Wolof Українська ქართული Magyar Mooreالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው በላጩ? ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም ሁለት ነገሮችን ጠቀሱ። የመጀመሪያው: ድሃዎችን ማብላትን ማብዛት ነው። እዚህ ውስጥም ሶደቃ፣ ስጦታ፣ ግብዣ፣ የሰርግ ድግስ ይገባሉ። የማብላቱ በላጭነትም በረሃብና ኑሮ በተወደደበት ወቅት የጠነከረ ይሆናል። ሁለተኛው: አወቅከውም አላወቅከውም በሁሉም ሙስሊም ላይ ሰላምታን ማቅረብ ነው።فوائد الحديث
ሶሐቦች በዱንያም ሆነ በመጨረሻው ዓለም የሚጠቅመምን ጉዳይ ለማወቅ ያላቸውን ጉጉት እንረዳለን።
ሰላምታ ማቅረብና ምግብ ማብላት ሰዎች በሁሉም ወቅት የሚፈልጉት ስለሆነና በላጭ ስራ ከመሆኑ አንፃርበ ኢስላም ውስጥ ትልቅ ደረጃ ከሚሰጣቸው ተግባራት መካከል እንደሆኑ እንረዳለን።
በነዚህ ሁለት ጉዳዮች ንግግራዊም ተግባራዊም በጎነት ይሰበሰባሉ። ይህም የተሟላው በጎነት ነው።
እነዚህ ጉዳዮች ሙስሊሞች በመካከላቸው ሊኖራቸው ከሚገባው መስተጋብር ጋር የተያያዘ ሲሆን ሌላ ቦታ ደግሞ አንድ ባሪያ ከጌታው ጋር ሊኖረው ስለሚገባ መስተጋብር የሚገልፁ ጉዳዮች አሉ።
በሰላምታ መጀመር በሙስሊሞች መካከል ብቻ የተገደበ ሲሆን ካፊር በሰላምታ አይጀመርም።