إعدادات العرض
ፀሐይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት የሰገደ አንድም ሰው እሳት አይገባም።
ፀሐይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት የሰገደ አንድም ሰው እሳት አይገባም።
ከአቡ ዙሀይር ዑማረህ ቢን ሩአይበህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ፀሐይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት የሰገደ አንድም ሰው እሳት አይገባም።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Português සිංහල Nederlands অসমীয়া Tiếng Việt Kiswahili ગુજરાતી پښتو ไทย Hausa Românăالشرح
የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የፈጅርን ሶላትና የዐስርን ሶላት የሰገደና በመስገድም የዘወተረ አንድም ሰው (የጀሀነም) እሳት እንደማይገባ ተናገሩ። እነዚህን ሁለት ሶላቶች የለዩት ከባባድ ሶላቶች ስለሆኑ ነው። የሱብሒ ወቅት በጣፋጭ እንቅልፍ ወቅት የሚሰገድ ነው፤ የዐስር ወቅት ደግሞ ሰው በቀን ስራና ንግድ በሚጠመድበት ጊዜ የሚሰገድ ነው። ይህ አይነት ችግር ከመኖሩም ጋር እነዚህን ሁለት ሶላቶች የተጠባበቀ ሰው በተቀሩትም ሶላቶች ላይ መጠባበቁ አይቀርም።فوائد الحديث
የሱብሒና የዐስር ሶላቶችን ደረጃና በነርሱ ላይ መጠባበቅ እንደሚገባ እንረዳለን።
እነዚህን ሶላቶች የሚያከናውነው አብዛኛው ሰው ነፍሱ ከስንፍናና ይዩልኝ ያገለለች ሆና አምልኮም የሚወድ ይሆናል።
التصنيفات
የሶላት ትሩፋት