።" አሉ።

።" አሉ።

የምእመናን እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንዲህ ብላለች፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ኢብኑ ጁድዓን በጃሂሊያ (በድንቁርናው)ዘመን ዝምድናን የሚቀጥልና ሚስኪኖችን የሚመግብ ነበር። ይህ ይጠቅመዋልን?" አልኳቸው። እሳቸውም "አንድ ቀንም "ጌታዬ ሆይ! የምንዳው ቀን ወንጀሎቼን ማረኝ" ብሎ ስለማያውቅ አይጠቅመውም።" አሉ።

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከእስልምና በፊት የቁረይሽ ሹማምንቶች መካከል ስለነበረው ዐብደላህ ቢን ጁድዓን ተናገሩ። ከመልካም ሥራዎቹ መካከልም፦ ዝምድናውን የሚቀጥል፣ ለነሱ መልካም የሚሰራ፣ ሚስኪኖችን የሚመግብና ሌሎችም እስልምና እንዲተገበር ያነሳሳቸውን መልካም ስራዎች የሚሰራ ነበር። እነዚህ ተግባሮቹ ግን በአላህ በመካዱና አንድ ቀንም "ጌታዬ ሆይ! የምንዳው ቀን ለኔ ወንጀሎቼን ማረኝ" ባለማለቱ ምክንያት ለመጪው ዓለም አትጠቅመውም።

فوائد الحديث

የኢማን ትሩፋትና ስራዎች ተቀባይነት እንዲያገኙ መስፈርት እንደሆነ መገለፁ።

የክህደት መጥፎነትና መልካም ስራዎችን የሚያበላሽ እንደሆነ መብራራቱ።

ከሀዲያን በአላህና በመጨረሻው ቀን ስለማያምኑ በመጪው ዓለም ሥራዎቻቸው አይጠቅማቸውም።

የሰው ልጅ በክህደት ዘመኑ የሠራቸው መልካም ስራዎች በሚሰልም ወቅት የሚጻፍለትና በመልካም ስራዎቹ የሚመነዳ መሆኑን ፤

التصنيفات

ኢስላም, ክህደት (ኩፍር)