'ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ እንዲህ ይሉ ነበር

'ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ እንዲህ ይሉ ነበር

የሙጚራ ቢን ሹዕባ ጸሐፊ ከሆነው ወራድ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ሙጚራ ቢን ሹዕባ ወደ ሙዐዊያህ የሚጻፍን እንዲህ የሚል ደብዳቤ አጻፈኝ: 'ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ እንዲህ ይሉ ነበር ‹ላኢላሀ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር፤ አላሁመ ላማኒዐ ሊማ አዕጦይተ ወላሙዕጢየ ሊማ መነዕተ ወላ የንፈዑ ዘልጀዲ ሚንከልጀድ› ትርጉሙም 'ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ብቸኛና ለርሱ አጋር የሌለው ነው። ንግስናም ምስጋናም ለርሱ ነው። እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው። አላህ ሆይ! ለሰጠኸው ማንም ከልካይ የለውም። ለከለከልከውም ማንም ሰጪ የለውም። የክብር ባለቤትም ክብሩ ካንተ (ቅጣት) አያድንም።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሁሉም ግዴታ ሶላት በኋላ "ላኢላሀ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር፤ አላሁመ ላማኒዐ ሊማ አዕጦይተ ወላ ሙዕጢየ ሊማ መነዕተ ወላየንፈዑ ዘልጀዲ ሚንከልጀድ" "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ብቸኛና ለርሱ አጋር የሌለው ነው። ንግስናም ምስጋናም ለርሱ ነው። እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው። አላህ ሆይ! ለሰጠኸው ማንም ከልካይ የለውም። ለከለከልከውም ማንም ሰጪ የለውም። የክብር ባለቤትም ክብሩ ካንተ (ቅጣት) አያድንም።" ይሉ ነበር። ማለትም: የተውሒድ ቃል በሆነችው "ላኢላሀ ኢለሏህ" አረጋግጣለሁም አምናለሁም። ትክክለኛዋን አምልኮም ለአላህ አፅንቼ ከርሱ ውጪ ካሉ አካላቶችም ውድቅ አደርጋታለሁ። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም። እውነተኛውና የተሟላው ንግስና፣ የሰማያትና የምድር ባለቤቶችም ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ መሆኑን አረጋግጣለሁ። እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው። አላህ የወሰነው መስጠትም ይሁን መከልከል ማንም መላሽ የለውም። እርሱ ዘንድ የሀብት ባለቤት ሀብቱ አይጠቅመውም። ብቸኛ የሚጠቅመው መልካም ስራ ነው።

فوائد الحديث

ይህ ዚክር የተውሒድና የምስጋና ቃላቶችን የሰበሰበ ስለሆነ ከሶላቶች በኋላ ማለቱ እንደሚወደድ እንረዳለን።

ሱናን ወደ መተግበርና ማሰራጨት መቻኮል እንደሚገባ እንረዳለን።

التصنيفات

የሶላት አዝካሮች