إعدادات العرض
ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አስር ረከዓዎችን ሸምድጃለሁ።
ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አስር ረከዓዎችን ሸምድጃለሁ።
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አስር ረከዓዎችን ሸምድጃለሁ። እነርሱም ከዙህር በፊት ሁለት ረከዓ፣ ከዙህር በኋላም ሁለት ረከዓ፣ ከመጝሪብ በኋላ ቤታቸው ውስጥ ሁለት ረከዓ፣ ከዒሻእ በኋላም ቤታቸው ውስጥ ሁለት ረከዓ፣ ከሱብሒ ሶላት በፊት ሁለት ረከዓ ናቸው። የሱብሒ ወቅት ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ የማይገባባት ሰአት ነበረች። ስለሰአቲቱም ሙአዚኑ አዛን ያለ ጊዜና ጎህ የወጣ ጊዜ ሁለት ረከዓ ይሰግዱ እንደነበር ሐፍሷ ነገረችኝ።" በሌላ ዘገባ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጁመዓ ሶላት በኋላም ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር።"
[ሶሒሕ ነው።] [በሁሉም ዘገባዎቹ ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî Kiswahili සිංහල Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Tiếng Việt ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or नेपाली Malagasy Kinyarwanda Română తెలుగు Lietuvių Oromoo മലയാളം Nederlands Soomaali Shqip Српски Українська Deutsch ಕನ್ನಡ Wolof Mooreالشرح
ዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዺየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሸመደዱትን አስር የሱና ረከዓዎች ገለጹ። እነዚህ ሱናዎች "ሱነን አርረዋቲብ" (ከግዴታ ሶላት በፊት ወይም በኋላ የሚሰገዱ ሱና ሶላቶች) ተብለው ይጠራሉ። ሁለት ረከዓ ከዙህር በፊትና ሁለት ረከዓ ከዙህር በኋላ፤ ከመጝሪብ በኋላ ሁለት ረከዓ ቤታቸው ውስጥ፤ ሁለት ረከዓ ከዒሻ ሶላት በኋላ ቤታቸው ውስጥ፤ ከፈጅር በፊት ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር። ይህም አስር ረከዓ ሞላ። ከጁመዓ ሶላት በኋላም ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር።فوائد الحديث
እነዚህ ከፈርድ በፊትና በኋላ የሚሰገዱ ሶላቶች ተወዳጅ መሆናቸውንና በነርሱ ላይ መዘውተርም እንደሚወደድ እንረዳለን።
ሱና ሶላቶችን ቤት ውስጥ መፈፀም መደንገጉን እንረዳለን።