إعدادات العرض
አንዳችሁ ወንድሙን ያገኘ ጊዜ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ! በመካከላቸው ዛፍ ወይም ግድግዳ ወይም ድንጋይ ከጋረዳቸው ከዚያም ድጋሚ ቢያገኘው በድጋሚ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ።
አንዳችሁ ወንድሙን ያገኘ ጊዜ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ! በመካከላቸው ዛፍ ወይም ግድግዳ ወይም ድንጋይ ከጋረዳቸው ከዚያም ድጋሚ ቢያገኘው በድጋሚ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ወንድሙን ያገኘ ጊዜ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ! በመካከላቸው ዛፍ ወይም ግድግዳ ወይም ድንጋይ ከጋረዳቸው በኃላም ድጋሚ ቢያገኘው በድጋሚ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ።"
[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tagalog Hausa Kurdî Kiswahili Português සිංහල Nederlands অসমীয়া Oromoo Tiếng Việt پښتو ગુજરાતી ไทย Română മലയാളം नेपाली Malagasy Deutsch Кыргызча తెలుగుالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሙስሊም ሙስሊም ወንድሙን ባገኘው ጊዜ በርሱ ላይ ሰላምታን ማቅረብ እንደሚገባ አነሳሱ። አንድ ላይ እየተጓዙ እንኳ በመካከላቸው እንደዛፍ ወይም ግድግዳ ወይም ትልቅ ድንጋይ ከለያያቸው በኋላ በድጋሚ ቢያገኘው በርሱ ላይ ሰላምታን እንዲያቀርብ አነሳሱ።فوائد الحديث
ሰላምታን ማብዛትና ሁኔታዎች በተለዋወጡ ቁጥር ሰላምታን መደጋገም እንደሚወደድ እንረዳለን።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የሰላምታ ሱናን በማስፋፋትና በዚህም ላይ እንድንበረታ ያላቸውን ከፍተኛ ጥረት እናያለን። ይህም በሙስሊሞች መካከል መተሳሰርንና ውዴታን ስለሚያመጣ ነው።
ሰላምታ የተባለው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ የሚደረገው መጨባበጥ ሳይሆን (አስሰላሙ ዐለይኩም) ወይም (አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ) መባባልን ነው።
ሰላምታ ዱዓ ነው። ሙስሊሞች ቢደጋገም ራሱ ከፊሉ ለከፊሉ ዱዓ መደራረግ ያስፈልጋቸዋል።
التصنيفات
የሰላምታና የማስፈቀድ ስነ-ስርዓት