'ወንጀላቸውን ይፋ ከሚያደርጉ በስተቀር ሁሉም ህዝቦቼ ይማርላቸዋል።

'ወንጀላቸውን ይፋ ከሚያደርጉ በስተቀር ሁሉም ህዝቦቼ ይማርላቸዋል።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ 'ወንጀላቸውን ይፋ ከሚያደርጉ በስተቀር ሁሉም ህዝቦቼ ይማርላቸዋል። ይፋ ከማውጣትም መካከል ሰውዬው ምሽት ላይ አንድ ወንጀልን ይሰራል ከዚያም አላህ በርሱ ላይ (ወንጀሉን) ሸሽጎለት አንግቶ ሳለ ‹እከሌ ሆይ! ትናንት ምሽት እንዲህ እንዲህ ሰራሁ።› ይላል። ጌታው (ወንጀሉን) ሸሽጎለት አድሮ ሳለ የአላህን ግርዶሽ ከራሱ ላይ የሚገፍ ሆኖ ያነጋል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙስሊም ወንጀለኛ ወንጀሉን በፉከራና በብልግና ይፋ የሚያወጣ ካልሆነ በቀር የአላህን ይቅርታና ምህረት የማግኘት ተስፋ እንዳለው ገለፁ። ወንጀሉን ይፋ የሚያደርግ ግን ይቅርታ አይገባውም። ምሽት ላይ ወንጀል ይሰራል ከዚያም አላህ ሸሽጎለት አንግቶ ሳለ ለሌላ ሰው ትናንት የሆነች ወንጀልን እንደሰራ ይናገራል። ጌታው ሸሽጎለት አድሮ ሳለ የአላህን ግርዶሽ የገለጠ ሆኖ ያነጋል።

فوائد الحديث

አላህ በርሱ ላይ ከሸሸገለት በኋላ ወንጀልን ይፋ ማውጣት ፀያፍ መሆኑን እንረዳለን።

ወንጀልን ይፋ ማድረግ በአማኞች መካከል ብክለት እንዲሰራጭ ያደርጋል።

አላህ በዱንያ የሸሸገው ሰው በመጨረሻው አለምም ይሸሽገዋል። ይህም አላህ በባሮቹ ላይ ካለው እዝነት ስፋት ነው።

በወንጀል የተፈተነ ሰው ወንጀሉን በራሱ ሸሽጎ ወደ አላህ መመለስ ይገባዋል።

ወንጀላቸውን ይፋ የሚያደርጉ ሰዎች ወንጀል ትልቅ መሆኑን እንረዳለን። እነሱም ወንጀላቸውን ይፋ ማድረግን በማሰብ ለነፍሳቸው ይቅርታን ያስመለጡ ናቸው።

التصنيفات

ወንጀለኞችን ማውገዝ, ወንጀለኞችን ማውገዝ