የሚጋልብ ሰው ለእግረኛ ሰላምታን ያቅርብ፤ እግረኛ ለተቀማጭ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሰዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።'

የሚጋልብ ሰው ለእግረኛ ሰላምታን ያቅርብ፤ እግረኛ ለተቀማጭ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሰዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።'

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "የሚጋልብ ሰው ለእግረኛ ሰላምታን ያቅርብ፤ እግረኛ ለተቀማጭ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሰዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሰዎች መካከል "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱሁ" የሚለውን ሰላምታን የማቅረብ ስነ-ስርዓትን ጠቆሙ። ይኸውም ህፃን ለትልቅ፣ ጋላቢ ለእግረኛ፣ እግረኛ ለተቀማጭ፣ ጥቂት ቁጥር ያላቸው በብዙዎቹ ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።

فوائد الحديث

ሐዲሥ ላይ በመጣው መልኩ ሰላምታን ማቅረብ እንደሚወደድ እንረዳለን። ነገር ግን እግረኛ ለጋላቢ ወይም ከዚህም ውጪ ሐዲሡ ላይ ከተጠቀሰው በተቃራኒው ሰላምታ ቢያቀርብ ከበላጩና ከተሻለው ተቃራኒ ቢሆንም ይፈቀዳል።

በሐዲሡ ላይ በተጠቀሰው አፈፃፀም መልኩ ሰላምታን ማስፋፋት ውዴታንና ትስስርን ከሚያመጡ ነገሮች መካከል አንዱ ነው።

በሐዲሡ ላይ የተጠቀሱት ተመሳሳይና ተመጣጣኝ ከሆኑ በላጩ ሰው ሰላምታውን የሚጀምረው ነው።

የሰው ልጅ የሚያስፈልገውን ሁሉ በማብራራት ረገድ የሸሪዓን ምሉዕነት እንረዳለን።

የሰላምታን ስነ-ስርዓት ማስተማርና ለሁሉም የሚገባውን ሐቅ (መብት) መስጠት እንደሚገባ እንረዳለን።

التصنيفات

የሰላምታና የማስፈቀድ ስነ-ስርዓት