إعدادات العرض
ውልደት ክልክል የሚያደርገውን ጥቢ ክልክል ታደርጋለች።
ውልደት ክልክል የሚያደርገውን ጥቢ ክልክል ታደርጋለች።
ከዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ውልደት ክልክል የሚያደርገውን ጥቢ ክልክል ታደርጋለች።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Português සිංහල دری অসমীয়া پښتو O‘zbek Tiếng Việt Македонски Kiswahili ភាសាខ្មែរ ਪੰਜਾਬੀ తెలుగు ไทย Moore Magyar Azərbaycan ქართული ಕನ್ನಡ ગુજરાતી Українська Shqip Кыргызча Kinyarwanda Српски тоҷикӣ Wolof Čeština தமிழ் नेपाली മലയാളം kmr ms Lietuviųالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ውልደት እንደ ኻል (በእናት በኩል ያለ አጎት) ወይም ዐም (በአባት በኩል ያለ አጎት) ወይም ወንድም ወዘተ ክልክል እንደሚያደርገው ሁሉ ጥቢም የሚከለክል መሆኑን ገለፁ። ውልደት ሐላል የሚያደርገውን ህግጋትንም ጥቢም ሐላል ያደርገዋል።فوائد الحديث
ይህ ሐዲሥ በጥቢ ህግ ዙሪያ መርህ የሆነ ሐዲሥ ነው።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: (ውልደት ክልክል የሚያደርገውን ጥቢም ክልክል ታደርጋለች።) ማለታቸው ውልደት ፍቁድ የሚያደርገውን ነገር ጥቢም ፍቁድ ያደርገዋል ማለት ነው። ይህም በዑለማዎች ሁሉ ስምምነት መሰረት ጋብቻና ከጋብቻ ጋር የተያያዙ ክልከላዎችን የተመለከተ ነው። ክልከላው የሚመለከተውም በጠባው ልጅና በአጥቢዋ ልጆች መካከል ነው። እርስ በርስ መተያየት፣ ለብቻ ገለል ብለው መቀመጥና መገለጥ ከመፈቀዱ አንፃር እንደቅርብ ዘመድ ደረጃ ነው የሚተያዩት። ነገርግን የመወራረስ፣ ለአጥቢዋ ወጪ መቻል፣ አጥቢዋ ባሪያ ብትሆን ነፃ ማውጣት፣ የመግደል ጉማ ክፍያ መጋራት፣ ቂሳስን ውድቅ ማድረግና ሌሎች የተቀሩት የወላድ እናትነት ህግጋት ግን ጥቢን ተከትለው አይመጡም።
በጥቢ ክልክል የመደረጉ ብይን እስከሞት የዘወተረ ክልከላን ነው የሚያፀናው።
በሌሎች ሐዲሦች እንደተረጋገጠው በጥቢ ክልክል መደረጉ የሚረጋገጠው በታወቁ አምስት መጥባቶች ነው። እንዲሁም የጠባው በመጀመሪያ ሁለት አመቶች ውስጥ መሆን አለበት።
በዘር ምክንያት ከነርሱ ጋር መጋባት ክልክል የሆኑ አካላት: እናቶች ‐ እዚህ ውስጥም በእናትም ይሁን በአባት በኩል ያሉ አያቶች ከፍ ቢሉ እንኳ ይካተታሉ‐ ፣ ልጆች ‐ የልጅ ልጆችም ወደታች ቢወርዱ እንኳ ይካተታሉ ‐ ፣ እህቶች ‐ በአባት በእናት የሚገናኙም ይሁኑ ወይም በአንዳቸው በኩል የሚገናኙ ቢሆኑም ተመሳሳይ ነው ‐ ፣ የአባት እህት (አክስት) ‐ እዚህ ውስጥም ከአባት ጋር በአባት በእናት የሚገናኙ እህቶቹም ይሁን በአንዱ በኩል የሚገናኙ እህቶቹ ቢሆኑም ሁሉም የአባት እህቶች ይካተታሉ። ልክ እንደዚሁ የአያቶች እህቶችም ይካተታሉ ‐ ፣ የእናት እህት ‐ ከእናት ጋር በአባትና በእናት የሚገናኙ እህቶቿም ይሁን በአንዱ በኩል የሚገናኙ እህቶቿ ቢሆኑም ሁሉም የእናት እህቶች ይካተታሉ። ልክ እንደዚሁ የሴት አያቶች እህቶችም የአባት እናትም ይሁኑ የእናት እናት ይካተታሉ ‐ ፣ የወንድም ሴት ልጆች፣ የእህት ሴት ልጆች ‐ እዚህ ውስጥም የእህትና የወንድም የልጅ ልጆችም ይካተታሉ‐።
በዘር ምክንያት ከነርሱ ጋር መጋባት ክልክል የሆኑ ሴቶች በጥቢም ምክንያት ክልክል ይሆናሉ። ነገር ግን የወንድም የጡት እናት (ይህ ማለት የደም ወንድምህ የጡት እናት ላልጠባው ልጅ ጋብቻ አትከለከልም።) እና የራስ ልጅ የጡት እህት (የወለድከው ልጅ የጡት እህት ያንተ ሚስት አጥብታት የአንተ የጡት ልጅ እስካልሆነች ድረስ ለአንተ ጋብቻ አትከለከለም) አይከለከሉም።"
التصنيفات
ጥቢ