إعدادات العرض
'ንገሩኝ እስኪ! አንዳችሁ በር ላይ በየቀኑ አምስት ጊዜ የሚታጠብበት ወንዝ ቢኖር ይህ ከእድፉ ያስቀራል ትላላችሁን?
'ንገሩኝ እስኪ! አንዳችሁ በር ላይ በየቀኑ አምስት ጊዜ የሚታጠብበት ወንዝ ቢኖር ይህ ከእድፉ ያስቀራል ትላላችሁን?
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አሉ፦ "'ንገሩኝ እስኪ! አንዳችሁ በር ላይ በየቀኑ አምስት ጊዜ የሚታጠብበት ወንዝ ቢኖር ይህ ከእድፉ ያስቀራል ትላላችሁን?' ሶሐቦችም 'ከእድፉ አንዳችም አያስቀርም።' አሉ። እርሳቸውም 'ይህ የአምስቱ ሶላቶች ምሳሌ ነው። አላህ በሶላት ወንጀሎችን ያብሳል።' አሉ።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Português සිංහල Svenska ગુજરાતી Yorùbá Tiếng Việt Hausa Kiswahili پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Malagasy नेपाली Čeština Oromoo Română Nederlands Soomaali తెలుగు മലയാളം ไทย Српски Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Lietuviųالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በጧትም በማታም የሚሰገዱትን አምስቱ ሶላቶች ትናንሽ ወንጀሎችንና ኃጢአቶችን ማስማራቸውና ማስወገዳቸውን፤ አንድ ሰው በየቀኑ አምስት ጊዜ የሚታጠብበት በሆነ በሩ ላይ እንዳለ ወንዝ መሰሉት። ከእድፉና ቆሻሻው አንዳችም አይቀርምና።فوائد الحديث
ይህ ትሩፋት ትናንሽ ወንጀሎችን ብቻ በማስማር የተገደበ ነው። ትላልቅ ወንጀሎች የግድ ተውበት ያስፈልጋቸዋል።
አምስቱን ሶላቶች የመፈፀምና የእነርሱን መስፈርቶች፣ ማእዘናቶች፣ ግዴታዎችና ሱናዎችን የመጠባበቅን ትሩፋት እንረዳለን።
التصنيفات
የሶላት ትሩፋት