إعدادات العرض
ሁላችሁም እረኞች (ሀላፊ) ናችሁ። ስለምትጠብቁት ነገርም ትጠየቃላችሁ።
ሁላችሁም እረኞች (ሀላፊ) ናችሁ። ስለምትጠብቁት ነገርም ትጠየቃላችሁ።
ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሁላችሁም እረኞች (ሀላፊ) ናችሁ። ስለምትጠብቁት ነገርም ትጠየቃላችሁ። በሰዎች ላይ የተሾመ መሪ እረኛ (ሀላፊ) ነው። ስለነርሱም ይጠየቃል። ወንድ በቤተሰቡ ላይ እረኛ (ሀላፊ) ነው። ስለነርሱም ይጠየቃል። ሴት ልጅ በቧሏ ቤትና በልጆቹ ላይ እረኛ (ሀላፊ) ናት። ስለነርሱም ትጠየቃለች። ባሪያ በአለቃው ገንዘብ ላይ እረኛ (ሀላፊ) ነው። ስለርሱም ይጠየቃል። አዋጅ! ሁላችሁም እረኞች (ሀላፊ) ናችሁ። ስለምትጠብቁት ነገርም ትጠየቃላችሁ።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tagalog ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Português සිංහල Русский Svenska ગુજરાતી Yorùbá Tiếng Việt Kiswahili پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Malagasy नेपाली Čeština Oromoo Română Nederlands Soomaali తెలుగు ไทย മലയാളം Српски Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Lietuviųالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማህበረሰቡ ውስጥ በሚገኝ ሁሉም ሙስሊም ላይ የሚሸከመውና የሚጠብቀው ኃላፊነት እንዳለበት ተናገሩ። ኢማምና መሪ አላህ ባስጠበቃቸው ኃላፊነት እረኞች (ኃላፊዎች) ናቸው። በርሱ ላይም ሸሪዓቸውን መጠበቅ፣ በነርሱ ላይ ግፈኛ ከሆነ መጠበቅ፣ ጠላቶቻቸውን መታገልና ሐቃቸውን አለማጥፋት ይገባዋል። ወንድም ለቤተሰቡ ቀለብ በማሟላት፣ መልካም አኗኗር በማኖር፣ በማስተማርና ስርዓት በማስያዝ ላይ ኃላፊነት አለበት። ሴትም በባሏ ቤት ውስጥ ቤቱን ባማረ መልኩ በማስተናበርና ልጆቹን በማነፅ ላይ ኃላፊነት አለባት። ስለዚህም ትጠየቃለች። አገልጋይ ባሪያና ተቀጣሪም በአለቃው ገንዘብ ላይ በእጁ ያለውን የአለቃውን ገንዘብ በመጠበቅ፣ እርሱን በማገልገል ሀላፊ ነው። ስለዚህም ይጠየቃል። እያንዳንዱ ሰው አላህ በሰጠው ሀላፊነት ላይ እረኛ (ሀላፊ) ነው። እያንዳንዱም ሰው ስለ ሀላፊነቱ ይጠየቃል።فوائد الحديث
በአጠቃላይ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ተጠያቂነት ያለ ሲሆን ሁሉም በልኩ፣ በችሎታውና በሀላፊነቱ ልክ ተጠያቂ ው።
የሴት ኃላፊነት ትልቅ መሆኑን እንረዳለን። ይህም በባሏ ቤት እና በልጆቿ ላይ ያላትን ግዴታዎች መወጣት ስለሆነ ነው።