የምትናገረውና የምትጣራበት ጉዳይ መልካም ነው። ለሰራነው ፀያፍ ተግባር ማስማሪያ እንዳለው እንደው ብትነግረን?

የምትናገረውና የምትጣራበት ጉዳይ መልካም ነው። ለሰራነው ፀያፍ ተግባር ማስማሪያ እንዳለው እንደው ብትነግረን?

ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ በፊት አብዝተው ነፍስ የሚገድሉ፣ አብዝተው ዝሙት የሚሰሩ የነበሩ የሺርክ ባለቤት የሆኑ ሰዎች ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘንድ በመምጣት እንዲህ አሉ ' የምትናገረውና የምትጣራበት ጉዳይ መልካም ነው። ለሰራነው ፀያፍ ተግባር ማስማሪያ እንዳለው እንደው ብትነግረን?' {እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይግገዙት፤ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ህግ የማይገድሉት፤ የማያመነዝሩትም ናቸው።} [ፉርቃን:68] የሚለውና {በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ።»} [አዝዙመር: 53] የሚለው አንቀፅ ወረደች።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ከሙሽሪኮች የሆኑ ሰዎች ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጡ። አብዝተው የገደሉና የዘሞቱ ነበሩ። ለነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: የምትጣራው ኢስላምና አስተምህሮቶቹ መልካም ጉዳይ ነው። ነገር ግን የወደቅንበት ሺርክና ከባድ ወንጀል ለርሱ ማስማሪያ አለውን? ወንጀላቸው ከመብዛቱና ከመተለቁ ጋርም አላህ ከሰዎቹ ተውበታቸውን እንደተቀበለ የሚጠቁሙ ሁለት አንቀፆች ወረዱ። ይህ ባልነበር ኖሮ በክህደታቸውና ጥመታቸው ላይ ይቀጥሉ ነበር። ወደዚህ ሃይማኖትም አይገቡም ነበር።

فوائد الحديث

የኢስላም ትሩፋትና ልቅናውን እንረዳለን። ኢስላም ያለፈውን ወንጀል ያስምራል (ያወድማል)።

አላህ በባሮቹ ላይ ያለው እዝነት ስፋቱን፣ ምህረቱንና ይቅር ባይነቱን እንረዳለን።

የሺርክን ክልክልነት፣ ያለ ህግ ነፍስን የመግደልን ክልክልነት፣ የዝሙትን ክልክልነት፣ እነዚህን ወንጀሎች የሚዳፈር ላይ የመጣውንም ዛቻ እንረዳለን።

ከኢኽላስና መልካም ስራ ጋር የተቆራኘ እውነተኛ ተውበት በአላህ መካድንም ጨምሮ ሁሉንም ትላልቅ ወንጀሎች ያስምራል።

ከአላህ እዝነት ተስፋ መቁረጥ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

ኢስላም, የአንቀፆች ተፍሲር (ማብራሪያ)