إعدادات العرض
እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ ከናንተ ላይ የድንቁርና ዘመንን ኩራትና በአባቶች መኮፈስን አስወግዷል።
እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ ከናንተ ላይ የድንቁርና ዘመንን ኩራትና በአባቶች መኮፈስን አስወግዷል።
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መካ የተከፈተ እለት ለሰዎች ኹጥባ አደረጉ። እንዲህም አሉ ' እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ ከናንተ ላይ የድንቁርና ዘመንን ኩራትና በአባቶች መኮፈስን አስወግዷል። ሰዎች ሁለት አይነት ናቸው። በጎ፣ አላህን ፈሪና አላህ ዘንድ የተከበረ፤ አመፀኛ፣ ጠማማና አላህ ዘንድ የወረደ ናቸው። ሰዎች የአደም ልጆች ናቸው። አላህም አደምን ከአፈር ነው የፈጠረው። አላህ እንዲህ ብሏል፦ {እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ። እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ። አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው። አላህ ግልፅን አዋቂ ውስጥንም አዋቂ ነው።} [ሑጁራት: 13]'"
[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚና ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa తెలుగు Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली മലയാളം Bosanski Italiano ಕನ್ನಡ Kurdî Oromoo Română Shqip Soomaali Српски Українська Wolof Moore Tagalog Malagasy தமிழ் Azərbaycan فارسی ქართული 中文 Magyar Portuguêsالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መካ የተከፈተ እለት ለሰዎች ኹጥባ አደረጉ። እንዲህም አሉ፦ እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ ከናንተ ላይ የድንቁርናን ዘመን ኩራት፣ ትዕቢትንና በአባቶች መኮፈስን አስወግዷል። ሰዎች ሁለት አይነት ብቻ ናቸው። ወይ አማኝ፣ በጎ፣ አላህን ፈሪና ለአላህ ባሪያ የሆነ ነው። ይህ ግለሰብ ሰዎች ዘንድ የተከበረ ዘርና ጎሳ ባለቤት ባይሆን እንኳ አላህ ዘንድ የተከበረ ነው። ወይም ደግሞ ከሀዲ፣ አመፀኛና ጠማማ ነው። ይህም ስልጣንና ክብር ያለው ከተከበረ ዘር እንኳ ቢሆን አላህ ዘንድ ከምንም ነገር ጋር የማይስተካከል የተዋረደና የዘቀጠ ነው። ሰዎች ሁሉ የኣደም ልጆች ናቸው። አላህም ኣደምን ከአፈር ነው የፈጠራቸው። መሰረቱ ከአፈር የሆነ ደግሞ በራሱ ሊኮራና ሊደነቅ አይገባውም። የዚህም ማረጋገጫ እንዲህ የሚለው የአላህ ንግግር ነው፦ {እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ። እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ። አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው። አላህ ግልፅን አዋቂ ውስጥንም አዋቂ ነው።} [ሑጁራት: 13فوائد الحديث
በዘርና በጎሳ መኩራራት መከልከሉን እንረዳለን።