إعدادات العرض
እኔና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለታችንም ጀናባ ላይ ሆነን ከአንድ እቃ እየጨለፍን እንታጠብ ነበር። የወር አበባ ላይ በሆንኩ ወቅትም ሽርጥ እንዳደርግ…
እኔና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለታችንም ጀናባ ላይ ሆነን ከአንድ እቃ እየጨለፍን እንታጠብ ነበር። የወር አበባ ላይ በሆንኩ ወቅትም ሽርጥ እንዳደርግ ያዙኝና ከግንኙነት ውጪ የሆነን ጨዋታ እንጫወት ነበር።
ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ "እኔና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለታችንም ጀናባ ላይ ሆነን ከአንድ እቃ እየጨለፍን እንታጠብ ነበር። የወር አበባ ላይ በሆንኩ ወቅትም ሽርጥ እንዳደርግ ያዙኝና ከግንኙነት ውጪ የሆነን ጨዋታ እንጫወት ነበር። ኢዕቲካፍ ላይ በሆኑ ወቅት ጭንቅላታቸውን ወደኔ ያወጡልኝና የወር አበባ ላይ ሆኜም አጥባቸው ነበርኩ።"
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî Kiswahili සිංහල Svenska ગુજરાતી Yorùbá Tiếng Việt پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Malagasy नेपाली Čeština Oromoo Română Nederlands Soomaali తెలుగు മലയാളം Lietuvių Српски ไทย Kinyarwanda Shqip ಕನ್ನಡ Wolofالشرح
የአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ስለነበራት አንዳንድ ግላዊ ሁኔታዋ ተናገረች። ከዚህም ውስጥ: የጀናባ ትጥበትን ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ሁለቱም ከአንድ እቃ እየጨለፉ ይታጠቡ ነበር። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የወር አበባ ላይ ሆና ሳለ ለጨዋታ መቅረብ የፈለጉ ጊዜ ከእንብርት እስከ ጉልበቷ ያለውን ሰውነት እንድትሸፍን ያዟትና ከግንኙነት ውጪ ያለን ጨዋታ ይጫወቱ ነበር። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መስጂድ ውስጥ ኢዕቲካፍ ይገቡ ነበር። እናታችን ዓኢሻ በቤቷ ውስጥ የወር አበባ ላይ ሆና ሳለ ጭንቅላታቸውን ያወጡላትና ታጥባቸው ነበር።فوائد الحديث
አንድ ወንድ ከሚስቱ ጋር ከአንድ እቃ እየጨለፈ መታጠብ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
የወር አበባ ላይ ያለችን ሚስቱ ከብልቷ ውጪ የፍቅር ጫወታ እንደሚፈቀድና ሰውነቷም ንፁህ እንደሆነ እንረዳለን።
ከግንኙነት ውጪ ያለን ፍቅር በሚሰሩበት ወቅት ሽርጥ መልበሷ እንደሚወደድም እንረዳለን።
ወደ ክልክል ከመውደቅ የሚከለክሉ መንገዶችን መጠቀም እንደሚገባ እንረዳለን።
የወር አበባ ላይ ያለች ሴት መስጂድ መቀመጥ መከልከሏን እንረዳለን።
የወር አበባ ላይ ያለች ሴት እርጥብም ሆነ ደረቅ ነገሮችን መንካቷ እንደሚፈቀድ እንረዳለን። ከዚህም ውስጥ ፀጉርን ማጠብና ማበጠሯ ለአብነት ይጠቀሳል።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከቤተሰባቸው ጋር የነበራቸውን መልካም አኗኗር እንረዳለን።