إعدادات العرض
አላህና መልክተኛው አስካሪ መጠጥን፣ በክትን፣ አሳማንና ጣዖታትን ከመሸጥ ከልክለዋል።
አላህና መልክተኛው አስካሪ መጠጥን፣ በክትን፣ አሳማንና ጣዖታትን ከመሸጥ ከልክለዋል።
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እርሱ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መካ የተከፈተ ቀን መካ ውስጥ እንዲህ ሲሉ ሰማቸው: "አላህና መልክተኛው አስካሪ መጠጥን፣ በክትን፣ አሳማንና ጣዖታትን ከመሸጥ ከልክለዋል።" ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የበክት ሞራን በርሱ ጀልባዎቻችን ይለቀለቃሉ፣ ቆዳችንን እንቀባበታለን፣ ሰዎች በርሱ መብራትን በመስራት ይጠቀማሉ። ንገሩን እርሱም ክልክል ነውን?" ተባሉ። እርሳቸውም "በፍፁም እርሱም ክልክል ነው።" አሉና ቀጥለውም የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ ጊዜ እንዲህ አሉ "አላህ የሁዶችን ረገመ። አላህ ሞራን ከመጠቀም የከለከላቸው ጊዜ አሳምረው ሸጡትና የሸጡበትን ዋጋ በሉት።"
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî অসমীয়া Kiswahili Tagalog Tiếng Việt ગુજરાતી Nederlands සිංහල پښتو ไทย नेपाली Кыргызча മലയാളം Malagasy Svenska Română తెలుగుالشرح
ጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መካ በተከፈተበት ዓመት መካ ሳሉ እንዲህ ሲሉ ሰማቸው "አላህና መልክተኛው አስካሪ መጠጥን፣ በክትን፣ አሳማንና ጣዖታትን ከመሸጥ ከልክለዋል።" ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የበክት ሞራ መሸጥ ይፈቀድልናልን? ምክንያቱም በርሱ ጀልባዎቻችንን ይጠገኑበታል፣ ቆዳዎቻችንን እንቀባለን፣ ሰዎች በርሱ ኩራዞቻቸውን ያበሩበታል።" ተባሉ። እርሳቸውም "በፍፁም እርሱን መሸጥም ክልክል ነው።" አሉና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀጠል አድርገው እንዲህም አሉ: "አላህ አይሁዶችን ይርገማቸው ያጠፋቸውና አላህ በነርሱ ላይ የእንስሳ ሞራን የከለከለ ጊዜ አቅልጠው ቅባቱን ሸጡትና ዋጋውን በሉት።"فوائد الحديث
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "በክት፣ አስካሪ መጠጥና አሳማ ሁሉ መሸጥ ሙስሊሞች ባጠቃላይ ክልክል መሆኑን ተስማምተውበታል።"
ቃዲ እንዲህ ብለዋል: "በዚህ ሐዲሥ ውስጥ ከተጠቀሰው ሞራ መረዳት እንደሚቻለው መብላቱና መጠቀሙ የማይፈቀድ ነገር መሸጡም የሸጡበትን ዋጋ መብላቱም አይፈቀድም የሚለውን መርህ ከዚሁ ሐዲሥ የምንወስደው ቁምነገር ነው።"
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «የሐዲሡ አመጣጥ የሚጠቁመው አብዛኞቹ እንደተረጎሙት "ክልክል ነው" ያሉት መሸጡን እንጂ መጠቀሙን እንዳልሆነ ነው።»
ክልክልን ሐላል ለማድረግ የሚጠቀሙት ዘዴ ሁሉ ጥመት ነው።
ነወዊ እንዲህ ብለዋል: «ዑለማዎች እንዲህ ብለዋል: የሞተን (በክትን) መሸጥ የመከልከሉ ጥቅል ውስጥ የካፊር ሬሳን የገደልነውና ከሀዲያን ሊገዙት ወይም ተለዋጭ መክፈል የፈለጉ ጊዜ የመሸጥ ክልክልነትን ያካትታል። በሌላ ሐዲሥ ውስጥ እንደመጣው ነውፈል ቢን ዐብደላህ አልመኽዙሚን የኸንደቅ ቀን ሙስሊሞች ገድለውት ከሀዲዎች ለሬሳው አስር ሺህ ዲርሃም ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አመጡ እርሳቸው ግን ሬሳውን ሰጥተዋቸው ገንዘቡን አልተቀበሉም።
التصنيفات
መብላት የሚፈቀዱና የሚከለከሉ እንስሶችና በራሪዎች