ዱንያ መጣቀሚያ ናት። ከዱንያ መጣቀሚያዎች ምርጡ መልካም ሚስት ናት።

ዱንያ መጣቀሚያ ናት። ከዱንያ መጣቀሚያዎች ምርጡ መልካም ሚስት ናት።

ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ዱንያ መጣቀሚያ ናት። ከዱንያ መጣቀሚያዎች ምርጡ መልካም ሚስት ናት።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዱንያም ውስጧ ያሉ ነገሮችም በሙሉ ጊዜያዊ መጠቀሚያዎች ሆነው ከዚያም የሚጠፉ መሆናቸውን፤ በላጩ መጣቀሚያም ሲያያት የምታስደስተው፣ ሲያዛት የምትታዘዘው፣ ሲርቅ ነፍሷንና ንብረቱን የምትጠብቅ መልካም ሚስት መሆኗን ተናገሩ።

فوائد الحديث

አላህ ለባሮቹ ፍቁድ ባደረጋቸው የዱንያ መልካም ነገሮች ላይ ያለማባከንና ያለመኩራራት መጠቀም መፈቀዱን ፤

ባልን በጌታው አምልኮ ላይ ስለምታግዝ መልካም ሚስት በመምረጥ ላይ መነሳሳቱን ፤

ከዱንያ መጣቀሚያዎች ሁሉ ምርጡ አላህን በማምለክ ላይ የሆነ ወይም አላህን በማምለክ ላይ አጋዥ የሆኑ ነገር መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

የሴቶች ህግጋት