ከፀዳን በኋላ የሚወጣንን ድፍርስና ዳለቻ ቀለም ፈሳሽ እንደ ምንም ነገር አንቆጥረውም ነበር።

ከፀዳን በኋላ የሚወጣንን ድፍርስና ዳለቻ ቀለም ፈሳሽ እንደ ምንም ነገር አንቆጥረውም ነበር።

ከኡሙ ዐጢያህ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው: ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቃልኪዳን ተጋብታ ነበር። እንዲህ አለች: "ከፀዳን በኋላ የሚወጣንን ድፍርስና ዳለቻ ቀለም ፈሳሽ እንደ ምንም ነገር አንቆጥረውም ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ በዚሁ ቃል ሲዘግቡት ቡኻሪ ደግሞ (ከመፅዳት በኋላ) ከሚለው ጭማሪ ውጪ ዘግበውታል።]

الشرح

ሶሐቢዯ ኡሙ ዐጢየህ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና-በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘመን የነበሩ ሴቶች ከወር አበባ መፅዳትን ካዩ በኋላ ቀለሙ ወደ ጥቁር ወይም ወደ ዳለቻ ያዘነበለ ከብልት የሚወጣውን ፈሳሽ የወር አበባ አድርገው እንደማይቆጥሩትና ለርሱ ብለውም ሶላትና ፆም እንደማይተዉ ተናገረች።

فوائد الحديث

ከወር አበባ መፅዳት በኋላ ከሴት ብልት የሚወርደው ፈሳሽ በደሙ ምክንያት የመጣ ድፍርስና ዳለቻ ቀለም ፈሳሽ ቢኖረው እንኳ የወር አበባ ተደርጎ እንደማይቆጠር እንረዳለን።

በተለመደው የወር አበባ ጊዜ ድፍርስና ዳለቻ ቀለም ያለው ፈሳሽ መፍሰሱ በውሃ ተቀላቅሎ እስካልሆነ ድረስ በወቅቱ የፈሰሰ ደም ስለሆነ እንደወር አበባ ይቆጠራል።

ሴት ልጅ ከወር አበባ ከፀዳች በኋላ ዉዱእ ታደርግና ትሰግዳለች እንጅ ለድፍርስና ዳለቻ ቀለም ፈሳሽ ብላ ሶላትና ፆምን አትተውም።

التصنيفات

የወር አበባ፣ የወሊድ ደምና የበሽታ ደም