إعدادات العرض
ረመዳን የመጣ ጊዜ ዑምራ አድርጊ። በረመዳን የሚደረግ ዑምራ ሐጅ ከማድረግ ጋር ይስተካከላል።" አሏት።
ረመዳን የመጣ ጊዜ ዑምራ አድርጊ። በረመዳን የሚደረግ ዑምራ ሐጅ ከማድረግ ጋር ይስተካከላል።" አሏት።
ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኢብኑ ዐባስ በስሟ ጠርቶ ለነገረኝ እኔ ግን ስሟን ለራሳኋት አንዲት የአንሷር ሴት እንዲህ አሏት "ከኛ ጋር ሐጅ ከማድረግ የከለከለሽ ምንድን ነው?" እርሷም "እኛ ከሁለት ግመል በቀር ሌላ አልነበረንም። የልጇ አባትና ልጇ በአንዱ ግመል ላይ ሐጅ አደረጉበት፤ ውሃ የምናመላልስበትን አንድ ግመል ደግሞ ለኛ ተወልን።" አለች። እርሳቸውም "ረመዳን የመጣ ጊዜ ዑምራ አድርጊ። በረመዳን የሚደረግ ዑምራ ሐጅ ከማድረግ ጋር ይስተካከላል።" አሏት።
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî മലയാളം Kiswahili Português සිංහල دری Svenska অসমীয়া ไทย Yorùbá Кыргызча ગુજરાતી Malagasy नेपाली Oromoo Română Nederlands Soomaali پښتو తెలుగు Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Српски Wolofالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመሰናበቻ ሐጅ የተመለሱ ጊዜ ሐጅ ላላደረገች ከአንሷር ለሆነች ሴት "ከኛ ጋር ሐጅ ከማድረግ የከለከለሽ ምንድን ነው?" አሏት። ሁለት ግመል እንደነበራቸው፤ ባሏና ወንድ ልጇ በአንዱ ግመል ላይ ሐጅ እንዳደረጉና ሌላኛውን ደግሞ ከጉድጓድ ውሃ እንዲያመላልሱበት እንደተወላቸው በመንገር ያልሄደችበትን ምክንያቷን ገለፀችላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዑምራን በረመዳን ወር በመፈፀም የሚገኘው ምንዳ የሐጅን ምንዳ የሚስተካከል እንደሆነ ነገሯት።فوائد الحديث
በረመዳን ወር ዑምራ ማድረግ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
በረመዳን ውስጥ ዑምራ ማድረግ ሐጅ ከማድረግ ጋር በምንዳው ይስተካከላል እንጂ ግዴታ የሆነበትን ሐጅ ያስቀርለታል ማለት አይደለም።
የወቅቶች ትሩፋት (ክብር) መጨመር የሥራዎችንም ምንዳ እንዲጨምር ያደርጋል። ከዚህም ውስጥ በረመዳን የሚሠራ ሥራ አንዱ ነው።
التصنيفات
የሐጅና ዑምራ ትሩፋት