إعدادات العرض
ትልቁ ጂሃድ የሚባለው ግፈኛ ባለስልጣን ዘንድ ፍትሀዊ ንግግርን መናገር ነው።
ትልቁ ጂሃድ የሚባለው ግፈኛ ባለስልጣን ዘንድ ፍትሀዊ ንግግርን መናገር ነው።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ትልቁ ጂሃድ የሚባለው ግፈኛ ባለስልጣን ዘንድ ፍትሀዊ ንግግርን መናገር ነው።"
[Hasan/Sound by virtue of corroborating evidence] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Kiswahili Português සිංහල অসমীয়া ગુજરાતી Tiếng Việt دری Nederlands नेपाली پښتو ไทย Svenska മലയാളം Oromoo Кыргызча Română తెలుగు Lietuvių Malagasy ಕನ್ನಡ Српски ქართული Mooreالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአላህ መንገድ ከሚደረጉ የጂሃድ አይነቶች መካከል ጠቃሚውና ትልቁ እውነተኛና ፍትሀዊ ንግግርን ግፈኛና በደለኛ ባለስልጣን ወይም መሪ ዘንድ መናገር እንደሆነ ገለፁ። ምክንያቱም በመልካም የማዘዝና ከመጥፎ የመከልከል ትልቁን መገለጫ ነውና የሰራው። ይህም በንግግርም፣ በጽሑፍም፣ በተግባርም ይሁን ከዚህ ውጪ ባሉ ጥቅም የሚገኝበትና ጉዳት የሚወገድበት በሆነ በማንኛውም መልኩ ሊፈፀም ይችላል።فوائد الحديث
በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ከጂሃድ አይነቶች እንደሆነ እንረዳለን።
መሪን መምከር ከትላልቅ የጂሃድ አይነቶች አንዱ ነው። ነገር ግን በእውቀት፣ በጥበብና በማረጋገጥ መሆኑ ግዴታ ነው።
ኸጧቢይ እንዲህ ብለዋል: ይህ በላጩ ጂሃድ የሆነበትም ምክንያት ጠላትን የተዋጋ ሰው በተስፋና ስጋት መካከል ነው የሚሆነው። እንደሚያሸንፍም ሆነ እንደሚሸነፍ አያውቅም። የስልጣን ባለቤት ፊት ግን በእጁ የተሸነፍክ ሆነህ ነው የምትቀርበው፤ እርሱ ፊት እውነትን የተናገርክና በመልካም ያዘዝከው ጊዜ ራስህን ለጥፋት አጋርጠህና ነፍስህን ለሞት አዘጋጅተህ የምትቀርብ በመሆንህ ነው። ይህም ስጋቱ ያመዘነ ስለሆነ በላጩ የጂሀድ አይነት ሆነ። በላጩ ጂሀድ የሆነው መሪው ቃሉን ሰምቶ ቢቀበለው ጥቅሙ ለበርካታ ሰዎች ስለሚዳረስ በዚህም ጥቅም ስላለው ነው ያሉም አሉ።
التصنيفات
በመልካም የማዘዝና ከመጥፎ የመከልከል ደረጃ