የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት በሚከፍቱበት ወቅትና

የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት በሚከፍቱበት ወቅትና

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት በሚከፍቱበት ወቅትና ለሩኩዕ ተክቢራ በሚያደርጉ ጊዜ እጃቸውን በትከሻቸው ትይዩ ከፍ ያደርጉ ነበር። ልክ እንደዚሁ ከሩኩዕ ራሳቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜም እጃቸውን ከፍ ያደርጉ ነበር። "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ፣ ረበና ወለከል ሐምድ" ይሉም ነበር። ሱጁድ ላይ ግን ይህንን አያደርጉም ነበር።»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ውስጥ በሶስት ስፍራዎች በትከሻቸው ትይዩ እጃቸውን ከፍ ያደርጉ ነበር። የመጀመሪያው ወቅት: የመክፈቻ ተክቢራ ወቅት ሶላትን የጀመሩ ጊዜ ነው። ሁለተኛው: ለሩኩዕ ተክቢራ ያደረጉ ጊዜ ነው። ሶስተኛው: ጭንቅላታቸውን ከሩኩዕ ቀና ያደረጉና "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ ረበና ወለከል ሐምድ" ያሉ ጊዜ ነው። ሱጁድ ማድረግ በሚጀምሩበት ወቅትም ሆነ ከሱጁድ በሚነሱበት ወቅት ግን እጃቸውን ከፍ አያደርጉም ነበር።

فوائد الحديث

ሶላት ውስጥ እጆችን ከፍ ከማድረግ ጥበቦች መካከል: የሶላት ውበት መሆኑና አላህን ማላቂያ መሆኑ ተጠቃሽ ነው።

ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅ ከፍ የሚደረግበት አራተኛ ስፍራ መጥቷል። እሱም ከአቡ ሑመይድ አስሳዒዲይ እንደተወራውና አቡዳውድና ሌሎቹም በዘገቡት ሐዲሥ ባለሶስትና ባለአራት ረከዓ ሶላቶች ላይ የመጀመሪያውን ተሸሁድ ብለው (ለሶስተኛው ረከዓ) በሚቆምበት ወቅት ነው።

በተጨማሪ ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጃቸውን በጆሯቸው ትይዩ ጆሯቸውን ሳይነኩ ከፍ ያደርጉ እንደነበር መጥቷል። ይህም ማሊክ ቢን ሑወይሪሥ ባስተላለፉትና ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተክቢራ ያደረጉ ጊዜ እጃቸውን በጆሯዋቸው ትይዩ እስኪሆን ድረስ ከፍ ያደርጉት ነበር።"

" ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" እና "ረበና ለከል ሐምድ" አንድ ላይ የሚለው ኢማምና ብቻውን የሚሰግድ ሰው ብቻ ናቸው። ተከታይ የሆነ ሰው ግን "ረበና ወለከል ሐምድ" ብቻ ነው የሚለው።

ከሩኩዕ በኋላ "ረበና ወለከል ሐምድ" ማለት ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአራት የቃላት ይዘት የመጣ ሲሆን ይህቺም አንዷ ናት። በላጩ ግን አራቱንም የቃላት ይዘት ("ረበና ወለከል ሐምድ" ፤ "አልላሁምመ ረበና ወለከል ሐምድ" ፤ "ረበና ለከል ሐምድ" ፤ "አልላሁምመ ረበና ለከል ሐምድ") በመከታተልና በመሸምደድ አንዳንዴ በዚህ አንዳንዴ በዛ እያቀያየሩ ማለቱ ነው።

التصنيفات

የሶላት አሰጋገድ