إعدادات العرض
ውሻ ከአንዳችሁ እቃ የጠጣ ጊዜ (እቃውን) ሰባት ጊዜ ይጠበው።
ውሻ ከአንዳችሁ እቃ የጠጣ ጊዜ (እቃውን) ሰባት ጊዜ ይጠበው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ውሻ ከአንዳችሁ እቃ የጠጣ ጊዜ (እቃውን) ሰባት ጊዜ ይጠበው።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tagalog ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî Kiswahili සිංහල অসমীয়া ગુજરાતી Tiếng Việt Nederlands नेपाली پښتو ไทย Svenska മലയാളം Кыргызча Română తెలుగు Malagasy ಕನ್ನಡ Oromoo Српски ქართული Moore Kinyarwanda Magyarالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ውሻ እቃ ውስጥ ምላሱን ያስገባ ጊዜ እቃው ሰባት ጊዜ እንዲታጠብ አዘዙ። ከነዚህ ሰባት ትጥበቶች የመጀመሪያውን በአፈር ቀላቅሎ ይጠበው ይህም ከዛ በኋላ ውሃ በተደጋጋሚ እንዲፈስበት ነው። በዚህም ከነጃሳውና ከጉዳቶቹ የተሟላ መፅዳት ይገኛል።فوائد الحديث
የውሻ ምራቅ ከባድ ነጃሳ ነው።
ውሻ እቃ ውስጥ ምላሱን በመንከር መጠጣቱ እቃውንም ውስጡ ያለውን ውሃም ይነጅሰዋል።
በአፈር ማፅዳትና በውሃም ሰባት ጊዜ መደጋገም የውሻ ሽንት፣ ሰገራና ሌሎችም ውሻ ያቆሸሻቸው ነገሮች የሚፀዱበት አፀዳድ ሳይሆን በአፉ የነካ ጊዜ ብቻ የሚፈፀም የአፀዳድ አይነት ነው።
እቃ በአፈር የሚፀዳበት የአፀዳድ አፈፃፀም: እቃ ውስጥ ውሃ ያደርግና አፈር ይጨምርበታል። ቀጥሎ በዚህ ከአፈር ጋር በተቀላቀለ ውሃ የተነጀሰውን እቃ ያጥባል።
የሐዲሡ ግልፅ መልዕክት ሸሪዓ ቤታችን እንድናደርጋቸው የፈቀዳቸውን ውሻዎችንም ሳይቀር የአደን፣ የጥበቃ፣ ለአዝርእትና ከብቶች ጥበቃ የምናሳድጋቸውን ውሻዎች ይመስል ሁሉንም ውሻዎች ያጠቃልላል።
ሳሙናና እንዶድ የአፈርን ቦታ አይተኩም። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለይተው አፈር ብለው በግልፅ ስላስቀመጡ ነው።