إعدادات العرض
ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ አጋማሽ ነው።
ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ አጋማሽ ነው።
ከአቡ ኡማማ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዐምር ቢን ዐበሳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ እንደሰማቸው ነገረኝ: "ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ አጋማሽ ነው። በዚህ ወቅት አላህን ከሚያወሱ መሆን ከቻልክ ሁን!"»
[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Français Tiếng Việt සිංහල Hausa Kurdî Kiswahili Português தமிழ் Русский অসমীয়া ગુજરાતી Nederlands پښتو नेपाली ไทย മലയാളം Svenska Кыргызча Română Malagasy ಕನ್ನಡ Српски తెలుగు ქართულიالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጥራት የተገባው ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ ሲሶ በመሆኑ አንተ አማኝ ሆይ! በዚህ ወቅት ከሚያመልኩት፣ ከሚሰግዱ፣ ከሚያወሱ፣ በወንጀላቸው ከሚፀፀቱ ሰዎች መካከል ለመሆን ከተሳካልህና ከቻልክ በዚህ ወቅት አጅር መሸመትና መታገል የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ተናገሩ።فوائد الحديث
አንድ ሙስሊም በሌሊቱ የመጨረሻ ወቅት ላይ ዚክር እንዲያደርግ መነሳሳቱን እንረዳለን።
በተለያዩ ወቅቶች ዚክር ለማለት፣ ዱዓ ለማድረግና ለመስገድ አንዱ አምልኮ ከአንዱ እንደሚበላለጥ እንረዳለን።
"ጌታ ወደ ባሪያው እጅግ ቅርብ የሚሆነው" በሚለው ሐዲሥና "አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሆኖ ነው።" በሚለው ሐዲሥ መካከል ባለው ልዩነት ሚረክ እንዲህ ብለዋል: እዛኛው ላይ የተፈለገው ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው የሌሊቱ አጋማሽ ላይ ሲሆን እዚህኛው ላይ የተፈለገው ደግሞ አንድ ባሪያ ካሉት ሁኔታዎች መካከል ወደ ጌታ የሚቀርበው በሱጁድ ሁኔታው መሆኑን ለመግለፅ ነው።