?የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ አድርገው ድምፃቸውን ይቀንሱበት ነበር።

?የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ አድርገው ድምፃቸውን ይቀንሱበት ነበር።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ አድርገው ድምፃቸውን ይቀንሱበት ነበር።»

[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ: መጀመሪያ: ከአፋቸው ወይም ከአፍንጫቸው አንዳች ነገር ወጥቶ አብሯቸው የተቀመጠውን ላለማወክ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ ያኖራሉ። ሁለተኛ: ድምፃቸውን ይቀንሱ ነበር። ከፍም አያደርጉትም።

فوائد الحديث

በማስነጠስ ዙሪያ የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መመሪያ መገለፁና በዚህ ጉዳይ እርሳቸውን መከተል እንደሚገባ እንረዳለን፤

አንድ ሰው ያስነጠሰ ጊዜ ከርሱ አንዳች ነገር ወጥቶ አብሮ የተቀመጠውን እንዳያውክ ልብስን ወይም መሀረምና የመሳሰሉትን አፍና አፍንጫ ላይ ማኖር እንደሚወደድ እንረዳለን።

ሲያስነጥሱ ድምፅን ዝግ ማድረግ የሚፈለግ ጉዳይ ነው። ይህም ስነ-ስርዓትን ከሚያሟሉና ከመልካም ስነ‐ምግባር የሚመደብ ነው።

التصنيفات

የማስነጠስና የማዛጋት ስነ-ስርዓት, የነቢዩ ሙሐመድ ስነ-ተፈጥሮ