አንድ ሰውዬ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በግራ እጁ በላ። እርሳቸውም 'በቀኝህ ብላ።' አሉት። እርሱም 'አልችልም!' አላቸው። እርሳቸውም…

አንድ ሰውዬ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በግራ እጁ በላ። እርሳቸውም 'በቀኝህ ብላ።' አሉት። እርሱም 'አልችልም!' አላቸው። እርሳቸውም 'አያስችልህ!' አሉት።

ከሰለማ ቢን አክወዕ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው፦ "አንድ ሰውዬ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በግራ እጁ በላ። እርሳቸውም 'በቀኝህ ብላ።' አሉት። እርሱም 'አልችልም!' አላቸው። እርሳቸውም 'አያስችልህ!' አሉት። ኩራት እንጂ ሌላ አልከለከለውም። ሰለማ እንዲህ አለ '(ከዛ በኃላ) እጁን ወደ አፉ ማንሳት አልቻለም።' "

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ሰው በግራ እጁ ሲበላ ተመለከቱትና በቀኝ እጁ እንዲበላ አዘዙት። ሰውዬውም በኩራትና በውሸት በቀኝ እጁ መብላት እንደማይችል መለሰላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በቀኝ እጁ መመገብ አሏህ እንዳያስችለው በርሱ ላይ ዱዓ አደረጉበት። ቀኝ እጁን ሽባ በማድረግ አላህ የነቢዩን ዱዓ ተቀበለ። ከዚህ በኋላም ምግብ ወይም መጠጥ ወደ አፉ ማንሳት አልቻለም።

فوائد الحديث

በቀኝ እጅ መብላት ግዴታ መሆኑንና በግራ መብላት ክልክል መሆኑን እንረዳለን።

የሸሪዓን ህግጋት ተግባራዊ ከማድረግ መኩራራት ባለቤቱን ለቅጣት የተገባ ያደርገዋል።

አላህ ለነቢዩ ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዱዓቸውን በመቀበል ማክበሩን እንረዳለን።

በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል በሁሉም ሁኔታ ላይ በመመገብ ወቅት እንኳ ሳይቀር መደንገጉን እንረዳለን።

التصنيفات

የመብላትና የመጠጣት ስነ-ስርዓት, የመብላትና የመጠጣት ስነ-ስርዓት