በአላህ መንገድ የሚዘምትን ያሰናዳ ሰው በርግጥም ዘምቷል። በአላህ መንገድ ለዘመተ ሰው (ቤተሰብ) በመልካም ትብብሩ የተተካ በርግጥም ዘምቷል።

በአላህ መንገድ የሚዘምትን ያሰናዳ ሰው በርግጥም ዘምቷል። በአላህ መንገድ ለዘመተ ሰው (ቤተሰብ) በመልካም ትብብሩ የተተካ በርግጥም ዘምቷል።

ከዘይድ ቢን ኻሊድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በአላህ መንገድ የሚዘምትን ያሰናዳ ሰው በርግጥም ዘምቷል። በአላህ መንገድ ለዘመተ ሰው (ቤተሰብ) በመልካም ትብብሩ የተተካ በርግጥም ዘምቷል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአላህ መንገድ ለሚዘምት ሰው መሳሪያ፣ መጓጓዣ፣ ምግብ፣ ቀለብና ሌሎችም ለጉዞው የግድ የሚያስፈልገውን ነገር ያሰናዳ ሰው ልክ እንደዘማቹ እንደሚቆጠርና የዘማቾቹን ምንዳ እርሱም እንደሚያገኝ ተናገሩ። የዘማችን ጉዳይ በመልካም ሊሸፍን ሃላፊነት የወሰደ ሰውና እርሱ (ዘማቹ) በራቀበት ወቅት ቤተሰቦቹን ሊንከባከብ የርሱን ቦታ የተተካ ሰውም ልክ እንደዘማች እንደሚቆጠር ተናገሩ።

فوائد الحديث

በመልካም ነገር ላይ በመተጋገዝ ላይ ሙስሊሞች መነሳሳታቸውን እንረዳለን።

ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ለሙስሊሞች ጥቅም ለመስራት ወይም የነርሱን መሰረታዊ ጉዳይ በመሸፈን ለቆመ ሰው መልካም ማድረግን የሚያነሳሳ መልዕክት አለው።»

አጠቃላይ መርህ: አንድ ግለሰብን ከአላህ አምልኮዎች መካከል በአንድ አምልኮ ያገዘ ሰው ከሰሪው ምንዳ ምንም ሳይቀነስ የሰሪውን ያህል ምንዳ ለአጋዡም ይኖረዋል።

التصنيفات

የጂሃድ ትሩፋት