አንድ ሰው በታመመ ወይም ጉዞ በወጣ ወቅት ሀገሩ እያለና ጤናማ ሳለ እንደሚያደርገው አጅር ይጻፍለታል።

አንድ ሰው በታመመ ወይም ጉዞ በወጣ ወቅት ሀገሩ እያለና ጤናማ ሳለ እንደሚያደርገው አጅር ይጻፍለታል።

ከአቡ ሙሳ አል-አሽዓሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ "አንድ ሰው በታመመ ወይም ጉዞ በወጣ ወቅት ሀገሩ እያለና ጤናማ ሳለ እንደሚያደርገው አጅር ይጻፍለታል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለአሏህ እዝነትና ችሮታ እየነገሩን ነው። ይህም አንድ ሙስሊም በሀገሩ እና ጤነኛ ሳለ ልምድ ያደረገው መልካም ስራ ከዚያም ችግር ገጥሞት ታሞ ማድረግ ባይችል፣ ወይም በጉዞ ወይም ደግሞ በሌላ በየትኛውም በቂ ምክንያት ሳያደርገው ቢቀር ልክ ጤነኛና በሀገሩ ሆኖ ሲያደርግ እንደነበረው ምንዳ ሙሉ ሆኖ ይጻፍለታል።

فوائد الحديث

አሏህ በባሮቹ ላይ ያለው ችሮታ ስፋቱን እንረዳለን።

ጤነኛ በሆንን እና ትርፍ ጊዜ ባገኘንበት አጋጣሚ መልካም ተግባርና ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም መበርታት እንደሚገባን እንረዳለን።

التصنيفات

የኢስላም ደረጃና ውበቶቹ