የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በፍርድ አሰጣጥ ዙሪያ ጉቦ ሰጪንም ተቀባይንም ረገሙ።

የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በፍርድ አሰጣጥ ዙሪያ ጉቦ ሰጪንም ተቀባይንም ረገሙ።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በፍርድ አሰጣጥ ዙሪያ ጉቦ ሰጪንም ተቀባይንም ረገሙ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጉቦ በሚሰጥ፣ በሚቀበልና በሚበላ ሰው ላይ ከአላህ እዝነት እንዲርቅና እንዲባረር ዱዓ አደረጉበት። ከዚህም መካከል ጉቦ ሰጪው ያለአግባብ ወደፍላጎቱ ለመዳረስ ሲል ለዳኞች በተሾሙበት ፍርድ እንዲያዘነብሉ (ኢፍትሃዊ እንዲሆኑ) የሚሰጠው ጉቦ እዚህ ውስጥ ይመደባል።

فوائد الحديث

ጉቦ መስጠት፣ መቀበል፣ አገናኝ መሆንና ተባባሪ መሆን በተሳሳተ ነገር ላይ መተባበር ስለሆነ ክልክል ነው።

የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጉቦ ተቀባይንም ሆነ ሰጪን ስለረገሙ ጉቦ ከትላልቅ ወንጀሎች የሚመደብ ነው።

ጉቦ በዳኝነትና ፍርድ ላይ ከሆነ የተከናወነው በውስጡ አላህ ካወረደው ፍርድ ውጪ በግፍ መፍረድም ስላለው ከባድ ወንጀልና አደገኛ ኃጢአት ይሆናል።

التصنيفات

የዳኛ ስነ-ስርዓት