መላእክት ውሻ እና ቃጭል ካላቸው መንገደኞች ጋር አብረው (አይጎዳኙም) አይሄዱም።

መላእክት ውሻ እና ቃጭል ካላቸው መንገደኞች ጋር አብረው (አይጎዳኙም) አይሄዱም።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "መላእክት ውሻ እና ቃጭል ካላቸው መንገደኞች ጋር አብረው (አይጎዳኙም) አይሄዱም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በጉዞ ወቅት በመካከላቸው ውሻ ካለ ወይም በእንስሶች ላይ የሚንጠለጠለውና ሲንቀሳቀስ ድምፅ የሚያወጣው ቃጭል ካለ መላእክት ከነርሱ ጋር በወዳጅነት እንደማይጎዳኙ ተናገሩ።

فوائد الحديث

ከአደን ውሻና ከጥበቃ ውሻ በቀር ውሻ መያዝና መጎዳኘት መከልከሉን እንረዳለን።

ከመጎዳኘት የሚቆጠቡት መላእክቶች የእዝነት መላእክት ናቸው። የሰውን ስራ የሚቆጣጠሩት መላእክት ግን ባሮችን ቤታቸውም ውስጥ ሆነው ጉዞም ላይ አይለዩዋቸውም።

ቃጭል መከልከሉን እንረዳለን። ምክንያቱም እርሱ ከሰይጣን መዝሙሮች መካከል አንዱ ነውና። ቃጭል በውስጡ የክርስቲያኖች ደወል ጋር መመሳሰልን ያቀፈ ነው።

አንድ ሙስሊም መላእክትን የሚያርቅ ከሆነ ነገር ሁሉ በመራቅ ላይ ሊጓጓ እንደሚገባ እንረዳለን።

التصنيفات

መላእክት