إعدادات العرض
የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጂሀድን እጅግ በላጭ ስራ አድርገን ነው የምናስበውና እኛም (ሴቶች) ከሀዲያንን እንታገልን?" እርሳቸውም፦ "በፍፁም! ነገር ግን እጅግ በላጩን ጂሀድ (ታገሉ!) (እርሱም)…
የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጂሀድን እጅግ በላጭ ስራ አድርገን ነው የምናስበውና እኛም (ሴቶች) ከሀዲያንን እንታገልን?" እርሳቸውም፦ "በፍፁም! ነገር ግን እጅግ በላጩን ጂሀድ (ታገሉ!) (እርሱም) ተቀባይነት ያለው ሐጅ ነው።" አሉ።
ከምእመናን እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጂሀድን እጅግ በላጭ ስራ አድርገን ነው የምናስበውና እኛም (ሴቶች) ከሀዲያንን እንታገልን?" እርሳቸውም፦ "በፍፁም! ነገር ግን እጅግ በላጩን ጂሀድ (ታገሉ!) (እርሱም) ተቀባይነት ያለው ሐጅ ነው።" አሉ።
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî മലയാളം Kiswahili Português සිංහල دری Svenska অসমীয়া ไทย Yorùbá Кыргызча ગુજરાતી Malagasy नेपाली Oromoo Română Nederlands Soomaali پښتو తెలుగు Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Српски Moore Lietuvių ქართული Українськаالشرح
ሰሐቦች (አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና) በአላህ መንገድ መታገልንና ጠላቶችን መጋደልን እጅግ በላጭ ከሆኑ ተግባራቶች መካከል እንደሆነ አድርገው ይመለከቱ ነበር። ዓኢሻም (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሴቶችም ጂሃድ ማድረግ ሊፈቀድላቸው ዘንድ ጠየቀች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሴቶች እጅግ በላጭ የሆነውን ጂሀድ ጠቆሟቸው: እርሱም ቁርኣንና ሐዲሥን የገጠመውና ከወንጀልና ከይዩልኝ የፀዳው ተቀባይነት ያለውን ሐጅ ነው።فوائد الحديث
ለወንዶች ጂሃድ እጅግ በላጭ ከሚባሉ ስራዎች መሆኑን እንረዳለን።
ለሴቶች ደግሞ ሐጅ ማድረግ ከጂሀድም ይበልጣል። ለሴቶች እጅግ በላጩ ተግባር ሐጅ ማድረግ ነው።
ሥራዎች እንደ ሠሪው ሁኔታ ይበላለጣሉ።
ሐጅ ጂሃድ (ትግል) ተብሎ የተጠራው ነፍስን መታገል ስለሆነ ነው። ሐጅ ለማድረግ ገንዘብና የሰውነት አቅም ያስፈልጋል። ሐጅ ልክ በአላህ መንገድ እንደመዋጋት አካላዊና ገንዘባዊ አምልኮ ነው።
التصنيفات
የሐጅና ዑምራ ትሩፋት