إعدادات العرض
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከክፍሏ ከማትወጣ ልጃገረድ የበለጠ አይነአፋር ነበሩ። አንዳች የሚጠሉትን ነገር የተመለከቱ ጊዜ ፊታቸው ላይ ነበር የምናውቀው።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከክፍሏ ከማትወጣ ልጃገረድ የበለጠ አይነአፋር ነበሩ። አንዳች የሚጠሉትን ነገር የተመለከቱ ጊዜ ፊታቸው ላይ ነበር የምናውቀው።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ ብለዋል: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከክፍሏ ከማትወጣ ልጃገረድ የበለጠ አይነአፋር ነበሩ። አንዳች የሚጠሉትን ነገር የተመለከቱ ጊዜ ፊታቸው ላይ ነበር የምናውቀው።»
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Kiswahili Português සිංහල অসমীয়া ગુજરાતી Tiếng Việt Nederlands پښتو नेपाली Hausa ไทย Svenska മലയാളം Кыргызча Română తెలుగు Malagasyالشرح
አቡሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሳታገባና ወንዶች ጋር ሳትኗኗር በቤቷ ተሸሽጋ ከምትኖር ልጃገረድ ሴት የበለጠ አይነአፋር እንደነበሩ ተናገረ። እጅግ አይነአፋር ከመሆናቸው የተነሳ አንድ ነገር የጠሉ ጊዜ ፊታቸው ይለዋወጣል እንጂ አይናገሩም። ይልቁኑም ባልደረቦቻቸው ፊታቸውን በመመልከት ያንን ነገር መጥላታቸውን ይረዳሉ።فوائد الحديث
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተላበሱት አይነአፋርነት መገለፁ። ይህ ባህሪም ትልቅ ስነምግባር ነው።
የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አይነአፋርነት የአላህ ክልከላ እስካልተደፈረ ድረስ ነው። የአላህ ክልከላ ከተደፈረ ግን ይቆጡ፣ ባልደረቦቻቸውንም የሚያዙና የሚከለክሉ ነበሩ።
የአይነአፋርነትን ባህሪ በመላበስ መነሳሳቱን እንረዳለን። አይነአፋርነት ነፍስ መልካም ተግባር እንድትሰራና ፀያፍን እንድትተው ይገፋፋታልና።